Search Course
Search through all lessons and sections in this course
Searching...
No results found
No matches for ""
Try different keywords or check your spelling
የአገልግሎት አመራር
Course Description
ኮርሱ በተለየ የተዘጋጀው ለክርስቲያን የአገልግሎት አመራሮች ሲሆን ነገር ግን ለየትኛውም የአመራር ሚና እንደ ግብአት ሊያገለግሉ የሚችሉ መርሆዎችን ይጠቀማል። እምነት ለምን የአመራር መሰረት እንደሆነ ያሳያል። መሪ ሊሆን ያለ ሰው ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት ችሎታውን እና ባህሪውን እንዴት ማዳበር እና ተፅዕኖውን እንዴት እንደሚያሳድግ ይማራል። መሪዎች ድርጅታቸውን እሴቶችን በማግኘት፣ ዓላማን መገንዘብ፣ ራዕይን በማጋራት፣ ግቦችን በማውጣት፣ ስልቶችን በማቀድ፣ እርምጃ መውሰድ፣ ስኬትን በመለማመድ ሂደት እንዴት መምራት እንደሚችሉ ይማራሉ።
Introduction
የኮርስ መግለጫዎች
ኮርሱ በተለየ የተዘጋጀው ለክርስቲያን የአገልግሎት አመራሮች ሲሆን ነገር ግን ለየትኛውም የአመራር ሚና እንደ ግብአት ሊያገለግሉ የሚችሉ መርሆዎችን ይጠቀማል። እምነት ለምን የአመራር መሰረት እንደሆነ ያሳያል። መሪ ሊሆን ያለ ሰው ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት ችሎታውን እና ባህሪውን እንዴት ማዳበር እና ተፅዕኖውን እንዴት እንደሚያሳድግ ይማራል። መሪዎች ድርጅታቸውን እሴቶችን በማግኘት፣ ዓላማን መገንዘብ፣ ራዕይን በማጋራት፣ ግቦችን በማውጣት፣ ስልቶችን በማቀድ፣ እርምጃ መውሰድ፣ ስኬትን በመለማመድ ሂደት እንዴት መምራት እንደሚችሉ ይማራሉ።
የኮርሱ አላማዎች
1. መሪነትን እንደ ግል ተፅዕኖ ለመግለፅ።
2. እምነት የመሪነት መሰረት እንደሆነ እውቅና ለመስጠት።
3. ለመሪዎች መፅሐፍ ቅዱሳዊ ብቃቶችን ለመማር።
4. ለሚመሩት በሚሆን መንገድ መምራት።
5. ለስኬት ቅድሚያ ሚሰጣቸውን ግላዊ ነገሮች ማስተዳደር።
6. ሰዎች ለድርጅቱ ግቦች ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ እንዲሆኑ ማነሳሳት።
7. ብድንን ለማዘጋጀት ለማሳደግ እና ለመምራት።
8. የድርጅትን ራዕይ፣ ግብ እና ስልት ለማቀድ።
9. በመሪነት ላይ ባህላዊ እይታዎችን ለመረዳት።
10. በንግግር፣ በጊዜ፣ በገንዘብ፣ እና አለባበስን በተመለከተ መርሆዎችን ተግባራዊ ለማድረግ።
ለክፍል መሪዎች የሆኑ አቅጣጫዎች
የውይይት ጥያቄዎች እና የክፍል ውስጥ እንቅስቃሴዎች በዚህ ምልክት ► ተጠቁመዋል። ለውይይት ጥያቄዎች የክፍል መሪው ጥያቄዎችን መጠየቅና ተማሪዎቹም በመልሱ ዙሪያ እንዲወያዩ ጊዜ መስጠት አለበት። አንድ ተመሳሳይ ተማሪ ብቻ በቅድሚያ መልስ የሚሰጥ ከሆነ ወይም አንዳንድ ተማሪዎች የማይናገሩ ከሆነ የክፍል መሪው ጥያቄውን ወደ አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ሊመራ ይችላል “ጳውሎስ ይህን ጥያቄ እንዴት ትመልሰዋለህ?”
ብዙ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል በኮርሱ ውስጥ ጥቅም ላይ ውሏል። በክፍል ውስጥ ጮክ ባለ ድምፅ ሊነበብ የሚገባቸው ምንባቦች በቀስት ነጥብ ተጠቁመዋል። በሌላ ጊዜ ደግሞ የመፅሐፍ ቅዱስ ማጣቀሻዎች በፅሁፍ ውስጥ በቅንፍ ተቀምጠዋል። ለምሳሌ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፥15)። ማጣቀሻዎቹ በፅሁፍ ውስጥ ላሉት መግለጫዎች ድጋፍ ናቸው። በቅንፍ ውስጥ ያሉትን ምንባቦች ሁልጊዜ ማንበብ አስፈላጊ አይደለም።
በአንዳንድ ምንባቦች ውስጥ የተካተቱ ከታሪካዊ መሪዎች የተወሰዱ ጥቅሶች አሉ። በክፍል ውስጥ ወደነዚህ ጥቅስ ሲደርሱ የክፍል መሪው አንድ ተማሪ ጥቅሱን እንዲያነብ እና እንዲያብራራ ሊጠይቅ ይችላል። እነዚህ መሪዎች ባደረጉትና ባስተማሩት ነገር መስማማት አይጠበቅብንም ነገር ግን ከምሳሌያቸው መማር እንችላለን።
እያንዳንዱ ትምህርት በስራዎች ይጠናቀቃል። ስራዎቹም ከቀጣዩ የትምህርት ጊዜ በፊት ተጠናቀው ሊቀርቡ ያስፈልጋል። ተማሪው ስራዎቹን ካልጨረሰ በኋላ ሊሰራው ይችላል። ይሁን እንጂ መሪው ተማሪዎች ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ በሚሰጣቸው ጊዜ ብቻ ስራዎችን እንዲጨርሱ ሊያበረታቱዋቸው ይገባል። በእያንዳንዱ ትምህርት ላይ የሚገኘው ስራ 3 ከትምህርቱ የተወሰኑ ነጥቦችን ማስታወስ ነው።
በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ መጀመሪያ ላይ ፦
- የክፍል መሪው ያለፈውን ትምህርት የፅሁፍ ስራዎች መሰብሰብ አለበት። መሪው ለስራ 1 የተፃፉትን አንቀፆች ለክፍል ውይይት ሊመርጥ ይችላል።
- እያንዳንዱ ተማሪ የስራ 3 ይዘትን ካለፈው ትምህርት በማስታወስ መፃፍ አለበት። በመቀጠልም እያንዳንዱ ተማሪ የእነርሱን ጥቅም እንዲረዳ ክፍሉ በታወሱ መግለጫዎች ዙሪያ ሊወያይ ይገባል።
ተማሪው ከShepherds Global Classroom የምስክር ወረቀት ማግኘት ከፈለገ ክፍለ ጊዜያትን መከታተል እና ስራዎችን ማጠናነቅ ይኖርበታል። የተጠናቀቁትን ስራዎች ለመመዝገብ በኮርሱ መጨረሻ ላይ ፎርም ተዘጋጅቷል።
አንዱ የኮርሱ አላማ ተማሪዎችን አስተማሪ እንዲሆኑ ማዘጋጀት ነው። የክፍል መሪው ተማሪዎች የማስተማር ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ዕድል መስጠት አለበት። ለምሳሌ የክፍል መሪው አልፎ አልፎ አንድ ተማሪ የትምህርቱን አጭር ክፍል ለክፍሉ እንዲያስተምር መፍቀድ አለበት።
ስብከት ትምህርት 17ን ይከተላል። ይህ የአመራር ስብከት በኮርሱ ውስጥ በማንኛውም ቦታ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል እና በቤተክርስቲያን ሊሰበክ ወይም የአመራር ብድኖች ሊማሩት ይችላሉ።
Shepherds Global Classroom የክርስቶስን አካል ለማነጽ በዓለም ዙርያ ለሚገኙ ክርስቲያን መሪዎች ሥርዓተ ትምህርትን ለመስጠት ያለመ ተቋም ነው። ዓላማችን አገር በቀል የኾኑ ማሠልጠኛ መርሓ ግብሮችን ለማብዛት 20 ትምህርቶች ያሉት ሥርዐተ ትምህርት መሣርያዎችን በማዘጋጀት በኹሉም አገራት ያሉ መንፈሳዊ አሰልጣኞች እጅ ላይ ተደራሽ ማድረግ ነው።
ይህ ትምህርት በነጻ በዚህ ማስፈንጠርያ ማግኘት ይቻላል https://www.shepherdsglobal.org/courses
ዋና ጸሐፊ፡ Dr. Stephen K. Gibson
የቅጂ መብት © 2024 Shepherds Global Classroom
የተተረጎመው ከ3ተኛ ቅጂ ከእንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመ
ሁሉም መብቶች የተጠበቁ ናቸው
በሌላ መልኩ ካልተገለፀ በስተቀር ሁሉም ቅዱሳት መጻህፍት ከ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™ መጽሐፍ ቅዱስ የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc. በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ። “Biblica” (ቢብሊካ)፣ “International Bible Society” (ዓለም ዐቀፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር) እና የቢብሊካ ዓርማ በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የፓተንት እና የንግድ ምልክት ቢሮ በBiblica, Inc., የተመዘገቡ የንግድ ምልክቶች ናቸው። በፈቃድ የሚወሰድ።
የፈቃድ መግለጫ
ይህ ትምህርት በሚከተሉት መርሖች ሥር በወረቀትም ኾነ በዲጅታል በመልኩ ታትሞ መሠራጨት ይችላል፤ (1) የትምህርቱ ይዘት በምንም መንገድ መለወጥ የለበትም፤ (2) ቅጂዎች ለትርፍ መሸጥ አይችሉም ፤(3) የትምህርት ተቋማት ይህን ትምህርት መጠቀም ሆነ ቅጂውን፥ የትምህርት ክፍያ ቢያስከፍሉም መጠቀም ይችላሉ፤ እና (4) ይህ ትምህርት ያለ Shepherds Global Classroom ፈቃድ እና ክትትል መተርጎም አይፈቀድም።
Ready to Start Learning?
Choose a lesson to begin your journey through this course.
Course Lessons
Print Course
SGC exists to equip rising Christian leaders around the world by providing free, high-quality theological resources. We gladly grant permission for you to print and distribute our courses under these simple guidelines:
- No Changes – Course content must not be altered in any way.
- No Profit Sales – Printed copies may not be sold for profit.
- Free Use for Ministry – Churches, schools, and other training ministries may freely print and distribute copies—even if they charge tuition.
- No Unauthorized Translations – Please contact us before translating any course into another language.
All materials remain the copyrighted property of Shepherds Global Classroom. We simply ask that you honor the integrity of the content and mission.
Questions? Reach out to us anytime at info@shepherdsglobal.org
Order Physical Course
የአገልግሎት አመራር
Total
$21.99Download Course
By submitting your contact info, you agree to receive occasional email updates about this ministry.
Additional Files
Audio Course Downloads
የአገልግሎት አመራር
Download audio files for offline listening
No audio files are available for this course yet.
Check back soon or visit our audio courses page.
Share This Course
የአገልግሎት አመራር
Share this free course with others