የአገልግሎት አመራር
የአገልግሎት አመራር

Search Course

Type at least 3 characters to search

Search through all lessons and sections in this course

Searching...

No results found

No matches for ""

Try different keywords or check your spelling

results found

Lesson 5: የአገልጋይ መሪነት

1 min read

by Stephen Gibson


የታላቅ መሪነት ሞዴል

ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻው እራት ያደረገው በፋሲካ በዓል ነው። በመደበኛ እራት ላይ አንድ አገልጋይ የእንግዶቹን እግር ማጠብ የተለመደ ነበር። ይህ ሥራ የሚሰጠዉ አብዛኛውን ጊዜ ከአገልጋዮቹ ዝቅተኛ ለሆነው ነበር።

በዚህ እራት ላይ ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ ብቻ ነበሩ። መጀመሪያ ላይ ማንም ሰው እግርን የማጠብ ስራ አልሰራም። ከደቀ መዛሙርቱ መካከል አንዳቸውም ለሥራው ፈቃደኛ አልነበሩም ምክንያቱም የአገልጋይነትን ቦታ አይፈለጉም። እያንዳንዳቸው አሁንም በአዲሱ መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ የስልጣን ቦታ ለማግኘት ተስፋ ያደርጉ ነበር።

በውስጣቸው እንዲህ እንደተባባሉ መገመት እንችላለን ጴጥሮስም በፀጥታ ዮሐንስን “እግሩን አንድ ሰው ሊያጥብለት ይገባል አንተ ማድረግ አለብህ” አለው፣ ምናልባትም ዮሐንስ “አይ እኔ አላደርገውም፤ ያዕቆብ ማድረግ አለበት” ሲል መልሶ ይሆናል። አንዳቸውም የአገልጋይነት ሚናን ለመውሰድ ፈቃደኛ አልነበሩም። በማዕድ መገባደጃ ላይ ኢየሱስ ተነስቶ ውሃና ፎጣ አንስቶ የእግር ማጠብን ሥራ ጀመረ። በእርግጥም ደቀ መዛሙርቱ ያፍሩ ነበር።

ጴጥሮስ መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ እግሩን እንዲያጥበው አልፈቀደለትም፤ ይህም ኢየሱስን በጣም ያከብረው ስለነበር ይህን የመሰለ ዝቅተኛ ሥራ እንዲሠራ አልፈለገም። ኢየሱስም ለጴጥሮስ እንዲህ አለው “ካላጠብሁህማ ከእኔ ጋራ እድል ፈንታ የለህም” (ዮሐንስ 13፥8)። ትንሹን ስራ የህይወቱን እና የሞቱን ታላቅ አላማ ለመወከል እየተጠቀመበት ነበር፤ ድነትን በመስጠት የሰው ልጆችን ሁሉ ለማገልገል። በሌላም ጊዜ እንዲህ አለ “የሰው ልጅ እንዲያገለግሉት ሳይሆን፣ ለማገልገልና ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ለመስጠት መጥቷልና” (ማቴዎስ 20፥28)። ከሞቱ ጋር የሰጠው አገልግሎት በሌሎች በርካታ የአገልግሎት ተግባራቶቹ የተወከለ ሲሆን በዚያን ጊዜ የነበረውን የእግር መታጠብን ጨምሮ ነበር። አንድ ሰው የኢየሱስን አገልግሎት የማይቀበል ከሆነ እርሱ የኢየሱስ መንግሥት አካል አይደለም።

ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ካጠበ በኋላ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው “ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?” (ዮሐንስ 13፥12)። በአለም ስርአት መሪው ለመገልገል እንደሚጠብቅ አስረድቷል። በእግዚአብሔር መንግሥት ግን መሪ ያገለግላል (ሉቃስ 22፥25-27)።

መምራት ሌሎችን ለማገልገል ተጽእኖን መጠቀም ነው፣ ትክክለኛው የአመራር ተነሳሽነት ይህ ነው። የሰዎችን ፍላጎት የሚከታተል እና ፍላጎቶቹን ለማሟላት መንገዶችን የሚፈልግ ሰው መሪ ይሆናል። ሰዎች ለእነሱ የሚያስብ እና ፍላጎታቸውን የሚያሟላ መሪ ይፈልጋሉ። ሰዎች ሥልጣንን ለእነርሱ ሲል ለሚጠቀም ሰው ሥልጣን ለመስጠት ፈቃደኛ ናቸው።

አንዳንድ ወታደሮች የእንጨት ቤት እየገነቡ ነበር። ከባድ ግንድ ለማንሳት እየታገሉ ነበር እና ሳጅናቸው እየጮኸባቸው ነበር። አንድ ሰው በአጠገባቸው እያለፈ ሳለ ለመመልከት ቆመ። ሳጅንን “ለምን አትረዳቸውም?” አለው። ሳጅን በንዴት “እኔ ሳጅን ነኝ” ሲል መለሰ።

ሰውዬው ከወታደሮቹ ጋር ተቀላቅሎ ግንድ እንዲያነሱ አገዛቸው እና ዩኒፎርሙን ለማሳየት ኮቱን ከፈተ። “እኔ ጄኔራል ነኝ”[1] አለ። General George Washington ነበረ። በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሆነ።

አንድ ደንበኛ አንድ ቀን ጠዋት ከትልቅ ባንክ ህንጻ ውጭ ባንኩ እስኪከፈት እየጠበቀ ነበር። አንድ ሰው መጣና መኪናውን አቆመ። ሰውየው በመኪና ማቆሚያ ቦታ ላይ አንዳንድ ቆሻሻዎችን አስተዋለ። ወደ ህንጻው ውስጥ እየገባ እነሱን ቆሻሻዎቹን ይጥላቸው ዘንድ አነሳቸው። ደንበኛው ወደ ውስጥ ሲገባ ቆሻሻ ያነሳውን ሰው አየ። ደንበኛውም አንድን ሰው “ይህ ሰውዬ ማነው?” ሲል ጠየቀው። መልሱ “እርሱ የባንኩ ፕሬዝዳንት ነው” የሚል ነበር። ፕሬዚዳንቱ ለባንኩ ስኬት እና መልካም ስም ቁርጠኛ ስለሆነ ምንም እንኳን ከፍተኛ ቦታ ላይ ቢሆኑም ቆሻሻን መሬት ላይ አይተዉም።

በአለም ስርአት ውስጥ እንኳን የማገልገል ፍላጎት ወደ እድገት ይመራል። ህዝቡ መሪውን የመምረጥ እድል ባገኘበት ቦታ ሊረዳን ይችላል እና ዝግጁ ነው ብለው የሚያስብትን ይመርጣሉ። መሪ ለፍላጎቶች ምላሽ በመስጠት ይነሳል፣ ሰዎች እርሱን ማዳመጥ ይጀምራሉ ምክንያቱም እርሱ እንደሚያስብላቸው እና በእሱ አመራር ሥር መልካም ነገር እንደሚሆንላቸው ስለሚገነዘቡ ነው።

የመሪዎች የማገልገል ሃላፊነት በአንዳንድ የስራ መደቦች ማዕረግ ይታወቃል። ለምሳሌ በታላቋ ብሪታንያ መንግሥት ውስጥ ከፍተኛው ቦታ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው፣ ትርጉሙ በጥሬው “የመጀመሪያ አገልጋይ” ማለት ነው። የታሪክ ታላላቅ መሪዎች የህዝብን ፍላጎት ያገለገሉ ናቸው። በዓለም ላይ ያሉ መሪዎች ሁልጊዜ የሚያገለግሉት ለትክክለኛ ዓላማ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የኢየሱስ ተከታይ በፈቃደኝነት፣ በትሕትና እና ሌሎችን ለመጥቀም ባለው ፍላጎት ማገልገል አለበት።

አንድ የኮሌጅ ፕሬዝደንት ብዙ ቦርሳዎችን ይዞ ቢሮው ደረሰ። አንድን ተማሪ እንዲረዳው ሲጠይቀው ተማሪው “አገልጋይ አይደለሁም” ሲል መለሰ። ሌላ ተማሪም ወዲያው “መርዳት እችላለሁ አገልጋይ ነኝ” አለ። ከብዙ አመታት በኋላ ሁለተኛው ተማሪ የኮሌጁ ፕሬዝዳንት ሆነ።


[1]ጄኔራል በማእረግ እና በስልጣን ከሳጅን እጅግ የላቀ ነው።