መግቢያ
በአንዳንድ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድር መልኩ ሁሉም ሰው መሪ መሆን አለበት። ለምሳሌ ሁሉም ወላጆች የራሳቸውን ልጆች መምራት አለባቸው። በዚህ ኮርስ ውስጥ የምናጠናቸው መርሆች በእነዚያ ተፈጥሯዊ የአመራር ቦታዎች ላይ ያለን ሰው ይረዳሉ። ሆኖም ይህ ኮርስ በአብዛኛው የሚያተኩረው እያንዳንዱ ሰው ሊሞላቸው ከሚገባቸው ተፈጥሯዊ ቦታዎች ባለፈ በአመራር መርሆዎች ላይ ነው።
Search through all lessons and sections in this course
Searching...
No results found
No matches for ""
Try different keywords or check your spelling
1 min read
by Stephen Gibson
በአንዳንድ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድር መልኩ ሁሉም ሰው መሪ መሆን አለበት። ለምሳሌ ሁሉም ወላጆች የራሳቸውን ልጆች መምራት አለባቸው። በዚህ ኮርስ ውስጥ የምናጠናቸው መርሆች በእነዚያ ተፈጥሯዊ የአመራር ቦታዎች ላይ ያለን ሰው ይረዳሉ። ሆኖም ይህ ኮርስ በአብዛኛው የሚያተኩረው እያንዳንዱ ሰው ሊሞላቸው ከሚገባቸው ተፈጥሯዊ ቦታዎች ባለፈ በአመራር መርሆዎች ላይ ነው።
[1]አንድ ሰው መሪ ለመሆን ለመፈለግ የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላል። ትክክለኛው ተነሳሽነት የማገልገል ፍላጎት ነው።
ስልጠና አንድን ሰው በእውቀት እና በችሎታ ከሌሎች የላቀ ያደርገዋል። በዋጋ ከሌሎች ሰዎች እንደሚበልጥ ሊሰማው ይችላል። እርሱ ከሌሎች ሰዎች ልዩ እንክብካቤን መጠበቅ ሊጀምር ይችላል የእርሱን ቦታ በተመለከተ ብቻ ሳይሆን በበላይነት ስሜት ምክንያት ነው።
ሐዋርያው ጳውሎስ “ዕውቀት ያስታብያል” ሲል አስጠንቅቋል (1ኛ ቆሮንቶስ 8፥1)። እውቀት መጥፎ ነገር ነው ወይም በራሱ ጎጂ ነው ማለቱ አልነበረም። በዚህ ክፍል ውስጥ ጳውሎስ የተናገረው አንዳንድ ነገሮችን የሚያውቅ ነገር ግን እውቀቱን በሚጠቀምበት መንገድ በፍቅር ስላልተገፋፋ ሰው ነው።
ስልጠና አንድን ሰው ለእግዚአብሔር መንግስት የበለጠ ውጤታማ ሊያደርገው ይችላል ነገር ግን ፍላጎቱ በትህትና ለማገልገል ከሆነ ብቻ ነው።
አንድ ሰው እንዴት ነው መሪ የሚሆነው? በግልፅ ስለሚሆን የስልጣን ቦታ ብቻ እያወራን አይደለም። መሪ ተጽእኖ ያለው ሰው ነው፤ ሰዎች የሚከተሉት ሰው ነው።
አንዳንድ ሰዎች የተወለዱት በሌሎች ላይ ተጽዕኖ የማድረግ ተፈጥሯዊ ችሎታ ይዘው ነው። በራስ መተማመንን ያሳያሉ፣ መፍትሄ ለማግኘት ፈጣን ናቸው እና ሰዎች በደመ ነፍስ ይከተሏቸዋል። እነዚህ ስብዕናዎች ስላሉ አንዳንድ ሰዎች ለመሪነት የተወለዱ እና ሌሎች አይደሉም ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ሆኖም ሰዎች መሪ የሚሆኑበት የተለያዩ መንገዶች አሉ።
እንደ አንድ የድሮ የዩክሬን አፈ ታሪክ አንድ ወጣት ወደ አንድ ቄስ ሄዶ እንዲህ አለ፡- “አባት ሆይ የ10,000 ሰዎች መሪ እንደሆንኩ በህልም አየሁ እውነት ይሆን?” ካህኑም “አሁን የቀረው 10,000ዎቹ ሰዎች አንተ መሪ እንደሆንክ ማለማቸው ብቻ ነው” አለው።
አንድ ሰው መሪ ሊሆን የሚችለው ከእነዚህ ምክንያቶች በአንዱ ወይም በአንዳንድ ጥምር ምክንያቶች ነው። አንድን ሰውን ለረጅም ጊዜ ውጤታማ መሪ ለማድረግ በሌሎች አካባቢዎች እጅግ በጣም የጎደለው ከሆነ ከእነዚህ ውስጥ አንዳቸውም ቢሆኑ በቂ አይደሉም።
(1) ግልጽ የተፈጥሮ ችሎታ
በራስ መተማመን ያለው የሚመስል ሰው በሄደበት ሁሉ ፈጣን መሪ ሊሆን ይችላል። የፈጠረውን መጠባበቅ ማሟላት ካልቻለ በመሪነት መቀጠል አይችልም። ተፈጥሯዊ ችሎታ ያለው ሰው እንኳን ውጤታማነቱን ለመቀጠል የአመራር መርሆዎችን መከተል አለበት።
(2) ለችግር የሚሰጥ ምላሽ
ብዙ መሪዎች ለችግር በተሰጠ ምላሽ የመጡ ናቸው። ታላቅ ችግር መሪን ይገልጣል። ለችግር የሚሰጥ ምላሽ በጥሪ ወይም ዝም ብሎ ከሚመለከተው እና ከሚያማርረው ሰው በሚቃረን መንገድ ከሀላፊነት ስሜት ሊመጣ ይችላል።
ችግር ለመሪው እድልን ያመጣል ነገር ግን ችግሩ ካለፈ በኋላ ለመምራት ሌሎች ባህሪያት አስፈላጊ ናቸው። አንዳንድ ጊዜ በችግር ጊዜ በደንብ የሚመራ ሰው በሌሎች ሁኔታዎች ጥሩ መምራት አይችልም።
(3) የረጅም ጊዜ አስተማማኝነት
አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰው ለብዙ አመታት አስተማማኝ እና ታማኝ ስለነበረ መሪ ነው። ለድርጅቱ ቁርጠኛ መሆኑን ስለሚያውቁ ሰዎች ያምኑታል።
(4) የተገኘ እውቀት
አንድ ሰው በአንድ የተወሰነ ዘርፍ እውቀትና ክህሎት ስላገኘ መሪ ሊሆን ይችላል። እርሱ በአንዳንድ ሁኔታዎች እና አንዳንድ ችግሮችን በመፍታት ላይ ብቻ አተኩሮ ሊመራ ይችላል።
(5) የመሪነት መርሆዎችን መማር
አንድ ሰው በዚህ ኮርስ ውስጥ በተጠኑት መርሆች መምራትን መማር ይችላል። ይሁን እንጂ ስልጠና ብቻውን አንድን ሰው አንዳንድ የተፈጥሮ ችሎታ ከሌለው በስተቀር በከፍተኛ ደረጃ ውጤታማ መሪ ሊያደርገው አይችልም።
(6) መለኮታዊ ጥሪ
እግዚአብሔር ሐዋርያትን፣ ነቢያትን፣ ወንጌል ሰባኪዎችን፣ እረኞችና አስተማሪዎችን ጠርቶአል (ኤፌሶን 4፥11)። አንዳንድ ጊዜ በተወሰኑ ቦታዎች ላይ በቤተክርስቲያን ውስጥ የመሪነት ተፅእኖ አላቸው። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች እግዚአብሄር የተፈጥሮ ችሎታ የሌለው የሚመስለውን ሰው ሲጠራ ይገረማሉ ነገር ግን እግዚአብሔር ሁል ጊዜ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ጥሪ ለመፈጸም የሚያስፈልገውን ችሎታዎች ይሰጣል።
ሰዎች አንድ መሪ ለአንድ አላማ ያደረ እና በእግዚአብሔር እርዳታ የተረዳ መሆኑን ካዩ ለሚያምኑበት አላማ ሊከተሉት ይችላሉ። ታማኝነታቸውንም ለመጠበቅ እሱ ብቃትን፣ አስተማማኝነትን እና መልካም ባህሪን ማሳየቱ አስፈላጊ ነው።
በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ በርካታ ሰዎች መሪነታቸውን እንዴት እንደጀመሩ እንመልከት።
ኤልሳዕን: በሽግግር ውስጥ መምራት
ኤልሳዕን ከኤልያስ በኋላ የእስራኤል መሪ ነቢይ እንዲሆን በእግዚአብሔር ተመርጧል። ከአንዱ ነቢይ ወደ ሌላው የሆነው የመሪነት ሽግግር በ1ኛ ነገሥት 19፡19-21 እና 2ኛ ነገሥት 2፡1-15 ላይ ተገልጧል።
የእግዚአብሔር ጥሪ ኤልሳዕን መሪ ያደረገው ግልጽ ምክንያት ነው። ሆኖም ሌሎች አስፈላጊ ዝርዝሮች አሉ። ኤልሳዕን ለአገልግሎት ራሱን ለማዋል ከአንድ ትልቅ እርሻ ለመውጣት ፈቃደኛ ነበር። የእግዚአብሔር ጥሪ ከሀብት ይልቅ ለኤልሳዕን አስፈላጊ ነበር። ከጊዜ በኋላ የኤልሳዕን ረዳት የሆነው ግያዝን ለገንዘብ ካለው ፍቅር የተነሳ የአገልግሎት ዕድሉን አጣ (2ኛ ነገሥት 5፡20-27)።
ኤልሳዕን የስልጠናው አካል ሆኖ አገልጋይ ለመሆን ፈቃደኛ ነበር። በትህትና ነብዩን እንደ ውሃ በመሸከም እና እሳትን በማቀጣጠል አገልግሏል (2ኛ ነገሥት 3፡11)። ያለዚህ ፈቃደኛነት በአገልግሎት አይሳካለትም ነበር።
ኤልሳዕ አሮጌው ነቢይ ኤልያስ አስደናቂ ነገሮችን በእግዚአብሔር ኃይል እንዳደረገ ያውቅ ነበር። ዝናብን ለሶስት አመት አቁሞ ነበር። የክፉውን ንጉሥና ንግሥት ሞት ተንብዮ ነበር። ከሰማይ እሳት እንዲወርድ ፀልዮ ነበር። ኤልሳዕን የወደፊት ሀላፊነቱን በሰዎች ዘዴዎች በመሰልጠን ሊወጣው እንደማይችል ያውቅ ነበር። የእግዚአብሔርን መንፈስ ቅባት እንደሚያስፈልገው ያውቃል።
ኤልያስ እግዚአብሔር ከወሰደው በኋላ ኤልሳዕን የኤልያስን መጎናጸፊያ አንሥቶ ውኃውን መታው እና “የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው?” አለ (2ኛ ነገሥት 2፡14)። ወጣቶቹ ነቢያት የአዲሱ መሪ አገልግሎት የእግዚአብሔር ኃይል ይኖረው እንደሆነ ለማየት ይጠባበቁ ነበር። ተአምሩን ባዩ ጊዜ “የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ ዐርፏል” አሉ (2ኛ ነገሥት 2፥15)። የእግዚአብሔርም ኃይል ከኤልያስ ወደ ኤልሳዕን መሸጋገሩን አይተዋል።
የአመራር ኃላፊነት ከአረጋውያን መሪዎች ወደ ታናናሾች መሸጋገሩ የማይቀር ነው። ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ኃይል ወዲያውኑ አይተላለፍም። አዲስ ትውልድ እምነት ከሌለው የእግዚአብሄርን ኃይል ያጣል እና በሰዎች ዘዴ ላይ የተመሰረተ ይሆናል።
ጌዲዮን: በችግሮች ውስጥ መምራት
ጌዴዎን በብሔሩ ወይም በጎሣው ውስጥ መሪ አልነበረም። የእርሱ ብሄር በየአመቱ በመከር ወቅት ይዘረፍ ነበር። ጌዲዮን ሁኔታውን ለመለወጥ ምንም ሀሳብ አልነበረውም የእግዚአብሔር መልእክተኛ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ ምግብን ለመደበቅ እየሞከረ ነበር። እርሱ በቀላሉ ለመትረፍ እና ሁኔታውን ለመቆጣጠር እየሞከረ ነበር። ይህ የመሪ ባህሪ አይደለም።
እግዚአብሔር ጌዲዮንን “ኀያል ጦረኛ” ሲል ጠራው ምክንያቱም እግዚአብሔር ማድረግ የሚችለውን ያውቃል (መሳፍንት 6፥12)። ጌዴዎን እግዚአብሔር እንደሚመርጠው በመገረሙ ብዙ ማረጋገጫ ምልክቶችን ጠየቀ።
ጌዲዮን የጣዖት አምልኮ ቦታን ባጠፋና ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ እግዚአብሔርን ታዘዘ። ድርጊቱ በዚያን ጊዜ ሃይማኖታዊ ለውጥ አላመጣም ነገር ግን ሰዎች የጣዖታትን ኃይል እንዲጠራጠሩ አድርጓል።
ጌዲዮን ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ይመካ ነበር። እንዲያውም አብዛኞቹን ሠራዊቶች ለመልቀቅ አምላክ የሰጠውን መመሪያ ታዘዘ። ጌዲዮን ያልተለመደ የጥቃት እቅድ አወጣ እና እግዚአብሔር ታላቅ ድልን ሰጠው።
እንደ አለመታደል ሆኖ ጌዴዎን ካሸነፈ በኋላ ህዝቡን እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ አልመራም ነገር ግን ወደ ጣዖት አምልኮ ተለወጠ። አንድ መሪ በረጅም ጊዜ ውስጥ የሚለዋወጥ ከሆነ ለእግዚአብሔር ያለውን ሙሉ ችሎታውን ማሳካት ይሳነዋል።
ነህምያ: በራዕይ መምራት
ነህምያ ከቤቱ ርቆ ለባቢሎን ንጉሥ ይሠራ የነበረ አይሁዳዊ ነበር። ስለ እየሩሳሌም ሁኔታ ሰማ። ከተማዋ ከረጅም ጊዜ በፊት በቁጥጥር ስር ውላለች። ግድግዳዎቹ ፈርሰዋል ይህም ማለት ህዝቡ በወራሪ ምህረት ላይ ነበር ማለት ነው።
ነህምያ እርምጃ ለመውሰድ የግል ኃላፊነት ተሰምቶት ነበር። ብዙ ሰዎች ምላሽ የመስጠት ግዴታ ሳይሰማቸው በዚህ ዜና አዝነዋል። ሁኔታውን ለመለወጥ እንችላለን ብለው አይጠብቁም ነበር። አንድ መሪ ሁኔታውን መለወጥ እንደሚቻል ስለሚያስብ ኃላፊነት ይሰማዋል። አንድን ነገር ማድረግ ስለሚችል የሆነ ነገርን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል።
ነህምያ የእግዚአብሔርን ጣልቃ ገብነት ለማግኘት ጸለየ። ነህምያ ያለ እግዚአብሔር እርዳታ ዳግም ግንባታው ሊከናወን እንደማይችል ያውቃል። ክርስቲያን መሪ ከራሱ ራዕይ ጋር እንዲስማማ አለምን ለመለወጥ የሚሞክር አይደለም ከእግዚአብሔር ረዕይ ጋር እንጂ፤ መተማመኑ በእግዚአብሔር እንጂ በሰው አይደለም።
እግዚአብሔር ልዩ እድልን ሰጠ። ንጉሱ የነህምያን ችግር ለመፍታት ፍላጎትን አሳየ። ከዚህ የምንማረው መርህ እኛን የሚረዱን ኃያላን ሰዎች እንደሚያስፈልጉን አይደለም። መርሁም የሚለው የእግዚአብሔር እቅድ ከሆነ እግዚአብሔር ግቡን ለመፈጸም ልዩ እድሎችን ይሰጣል።
ነህምያ ወደ ኢየሩሳሌም ደረሰና ራእዩን በዚያ ላሉት መሪዎች ገለጸላቸው። ራዕዩ የጀመረው በአንድ ሰው ነው ሌሎች ግን ብዙም ሳይቆይ ራዕዩን መካፈል ጀመሩ። መሪ ሁሉም ሰው ራእዩን ወዲያው እንዲረዳው መጠበቅ የለበትም። ድጋፍ የሚጀምረው በጥቂቶች ነው።
ራዕዩን የሚካፈሉ ጥቂት ሰዎች ሊኖሩት ይገባል አለበለዚያ መሪው ማንንም አይመራም። ራዕዩ በቁርጠኛ ብድን የተያዘ መሆን አለበት። ራዕዩን ባለቤት ማድረግ፤ ከርሱ ጋር ከመስማማት እና ሊከሰት ይችላል ብሎ ከመጠበቅ በላይ ነው። ራዕዩን የሚጋሩት ሰዎች ራዕዩ የራሳቸው እንደሆነ ሊሰማቸው ይገባል።
በራዕዩ ላይ ያለው ቁርጠኝነት ማህበረሰብን ፈጠረ። አብረው መኖር፣ መደጋገፍ እና ለራዕዩ ታማኝ ሆነው እንዴት መኖር እንደሚችሉ መማር ነበረባቸው።
ነህምያ በመጀመሪያ ለእነዚህ ችግሮች ምንም ሃላፊነት ባይኖረውም መሪ የሆነውን ሰው ምሳሌ ነው። የስልጣን ቦታን በማግኘት አልጀመረም ለውጥ ለማምጣት ባለው ፍላጎት እንጂ። በራዕዩ ምክንያት መሪ ሆነ።
ንጉስ ሳኦል፡ ከስልጣን ቦታው የሚመራ
ሳኦል የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ ነበር። ያለፈውን ንጉሥ ምሳሌ መከተል አልቻለም። ገበሬ ነበር እና ምንም አይነት የገዢነት ልምድ አልነበረውም።
ሲሾም ወታደሮች እና የመንግስት ሰራተኞች አልነበሩም። የመንግስት ስራዎችን ለመደገፍ ምንም አይነት ኦፊሺያል ዳኞች የመንግስት ቢሮዎች እና ታክስ አልነበረም። ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ከተሾመ በኋላ የሚጫወተው ሚና በጣም ግልጽ ስላልሆነ የግብርና ሥራ መስራቱን ቀጠለ።
በመቀጠልም አንድ ችግር ተከሰተ (1ኛ ሳሙኤል 11)። ከእስራኤል ጋር የሚተባበር አንድ ትንሽ ሕዝብ በእስራኤል ጠላቶች ተጠቃ። ሌላው ቀርቶ አዲሱ ንጉሥ ምንም ነገር ያደርጋል ብለው ስላልጠበቁ ወደ ሜዳ የሄደ ማንም አልነበረም። ሳኦል በቀኑ መገባደጃ ላይ ከእርሻ ሥራ ወደ ቤቱ ሲመለስ ዜናውን ሰማ።
ሳኦል በጥንካሬና በውሳኔ አደረገ። በሚያስደነግጥ መልኩ ባረሰባቸው በሬዎች ደም መልእክት ላከ (1ኛ ሳሙኤል 11:7)። አስቡት አንድ የሚሮጥ መልእክተኛ የጎሳ አለቃ ቤት ሲደርስ። የበሬውን በደም የተጨማለቀ እግር መሬት ላይ ጥሎ “ንጉሥ ሳኦል በዚህ ድንገተኛ አደጋ ለመርዳት በማይመጣ በማንኛውም ሰው በሬዎች ላይ እንዲህ ይደረጋል አለ” ሲል አስታወቀ።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሰብስበው ታላቅ ድልን አሸንፈዋል። ይህ ድል ሳኦልን እንደ ጠንካራ መሪ አድርጎታል።
ሳኦል ከስልጣን ቦታ መምራት የጀመረ መሪ ምሳሌ ነው። መጀመሪያ ላይ መሪ መሆን አልፈለገም ነገር ግን እሱ የስልጣን ቦታ ስለነበረው ኃላፊነቱ ተሰማው።
► ሳኦል ለተፈጠረው ችግር የሰጠው ምላሽ ከጌዴዎን የተለየ የሆነው እንዴት ነው?
አቅም እንዳለው መሪ እራስዎን እንዴት መገምገም ይችላሉ? ይህንን የአንድ መሪ ባህሪ ዝርዝርን አጥኑ። ከእነዚህ ውስጥ በአንዳንዶቹ ደካማ ከሆናችሁ በእግዚአብሔር እርዳታ ልታዳብሯቸው ትችላላችሁ። በነዚህ ዘርፎች እየጎለበቱ ሲሄዱ አመራርዎን ያጠናክራሉ።
ውጤታማ መሪ…
1. እሱን በሚያውቁት ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።
2. በግል ስነ ምግባር አለው።
3. ከዚህ ቀደም ኃላፊነቶችን ተወጥቷል።
4. አዲስ ኃላፊነት ለመውሰድ ፈቃደኛ ነው።
5. ከሰዎች ጋር ጥሩ ተግባቦት አለው።
6. ሌሎችን ለማገልገል ፈቃደኛ ነው።
7. ተነሳሽነትን ይወስዳል።
8. ታማኝ ነው።
9. ጭንቀትን መቋቋም ይችላል።
10. በንዴት አይሸነፍም።
11. አዎንታዊ መንፈስ አለው።
12. ከተስፋ መቁረጦች ያገግማል።
13. መተማመን አለው።
14. ቅንነት አለው።
15. ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ እያደገ ነው።
16. በግል ችግሮች ያልተያዘ።
17. የመማር ችሎታ እና መማርን ለመቀጠል ፍላጎት አለው።
18. ችግሮችን መፍታት ይችላል።
19. አሁን ባለው ሁኔታ አይረካም።
20. ለውጦችን ለማድረግ ፈቃደኛ ነው።
21. ትልቁን ምስል ይመለከታል።
22. ቀጥሎ ምን መደረግ እንዳለበት ማየት ይችላል።
እርስዎ ዋና መሪ ባልሆኑበት ድርጅት ውስጥ እየሰሩ ከሆነስ?
የድርጅታችሁ መሪ በዚህ ኮርስ ውስጥ የተማራችሁትን መርሆች እንዳይከተል የሚከለክው ገደብ ቢኖረውስ?
አንዳንድ ጊዜ ወጣት ታዳጊ መሪ የሚያውቃቸውን የአመራር መርሆች መተግበር እንደማይችል ስለሚሰማው ይበሳጫል። በሥልጣን ቦታ ላይ ስላልሆነ ችሎታው ውስን እንደሆነ ይሰማዋል።
አንዳንድ ጊዜ አንድ ወጣት መሪ የተወሰነ ሥልጠና ሲያገኝ ቤተክርስቲያኑን ወይም ድርጅቱን ወዲያውኑ እንደሚያሻሽል ይጠብቃል። በአዲሱ እውቀቱ ምክንያት በቀድሞዎቹ መሪዎች አሠራር ውስጥ ብዙ ስህተቶችን ይመለከታል። ሆኖም የሚያሳስባቸውን ነገር እንደሚጋራ እና ማገልገል እንደሚፈልግ በማሳየት እምነት ማግኘት አለበት። ጳውሎስ ወጣትነትህን ሰዎች እንዳይናቁ የምትከላከልበት መንገድ ጥሩ ምሳሌ መሆን ነው ብሏል “በንግግር እና በኑሮው፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንፅሕና” (1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥12)። አንድ ወጣት በጣም ቆራጥ ከሆነና ሃሳቡ እንደሚሠራ ለማሳየት የሚሞክር ከሆነ መሪዎቹ እንዳያምኑት ያደርጋቸዋል ምክንያቱም ጭንቀታቸውን የማይረዳ እና የማይሰማቸው ስለሚመስላቸው ነው። አንድ ወጣት መሪ ለቀድሞ መሪዎች የሚያሳስባቸውን ነገር እንደሚያስብ ለማሳየት ጊዜ ከወሰደ ለበለጠ ኃላፊነት እንዲያምኑት ያደርጋል።
መሪ ለመሆን የሚጠብቅ ሰው የአመራር መርሆችን ተግባራዊ ለማድረግ የስልጣን ቦታ ላይ እስኪቀመጥ ድረስ መጠበቅ የለበትም። ኃላፊነቶችን ከመወጣት፣ እምነትን ማሳደግ፣ እውቀቱን ማሳደግ፣ ክህሎትን ከመለማመድ፣ በአስተማማኝነቱ መልካም ስም ከማግኘት እና ከግል ጥቅሙ ይልቅ ለድርጅቱ ስኬት ያለውን ቁርጠኝነት ከማሳየት ጋር የተያያዙ መርሆችን ተግባራዊ ማድረግ ይችላል። እነዚህ ነገሮች ከእሱ በላይ ያሉትን መሪዎች ጨምሮ ከሁሉም ሰው ጋር ያለውን ተጽእኖ ይጨምራሉ።
አስታውሱ መሪ ማለት በቀላሉ ተፅዕኖ ያለው ሰው ነው። ያለ ኦፊሽያላዊ የስልጣን ቦታ ተጽእኖዎን የሚያዳብሩ ሌሎች ብዙ ነገሮች አሉ።
መሪ ለመሆን አዲስ ድርጅት መመስረት እንዳለብህ ለማሰብ አትቸኩል። ባለህበት ማድረግ የምትችለው ብዙ ነገር አለ።
ቦታዎ ምንም ይሁን ምን ወጣት መሪዎችን እና የቡድን አባላትን ማበረታታት እና መምከር ይችላሉ። ይህ በድርጅቱ ውስጥ እንደ መደበኛ የስራዎ አካል ሆኖ ሊከናወን ይችላል ወይም የእርስዎን እርዳታ ከሚያደንቁ ሰዎች ጋር መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሊከናወን ይችላል።
በድርጅትዎ ውስጥም ሆነ ውጭ ሌሎች እንዲመክሮት ይፈልጉ። አብዛኞቹ መሪዎች ጥበባቸውን ለማካፈል ደስተኞች ናቸው። በልዩ የአመራር ገጽታዎች ላይ ምክር ሊሰጥዎት ይችላል፤ መካሪው በሁሉም አካባቢ ፍጹም ምሳሌ መሆን አይጠበቅበትም። መካሪው በእድሜ ካንተ ሊያንስ እና በተወሰኑ አካባቢዎች የተካነ ሊሆን ይችላል።
► በዚህ ትምህርት ምክንያት ግቦችዎን ወይም ድርጊቶችዎን እንዴት እንደሚቀይሩ ይጠብቃሉ?
1. ከዚህ ትምህርት የህይወት ለውጥ የሚያመጣ ጽንሰ ሀሳብን የሚያጠቃልል አንቀፅ ይፃፉ። ለምን አስፈለጊ እንደሆነ ያብራሩ። ምን ጥሩ ነገር ሊያደርግ ይችላል? ባለማወቃችንስ ምን ጉዳት ሊያስከትል ይችላል?
2. የዚህን ትምህርት መርሆች እንዴት በራስዎ ህይወት ላይ እንደምትተገብሩ ያብራሩ። ይህ ትምህርት ግቦችዎን እንዴት ይለውጣል? ድርጊቶችዎንስ እንዴት ለመለወጥ አስበዋል?
3. በትምህርቱ ውስጥ የተዘረዘሩትን መሪን የሚያደርጉ ምክንያቶችን እና መሪ የመሆን አቅም ያለው ሰው ባህሪያትን አጥኑ። በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ መጀመሪያ ላይ ብዙዎቹን ምክንያቶች እና ባህሪያትን ከማስታወስ ለመፃፍ ዝግጁ ይሁኑ።
4. ከቀጣዩ ክፍለ ጊዜ በፊት ዮሐንስ 13፥1-17 ያንብቡ። ይህ ክፍል ስለ አመራር ምን እንደሚነግረን ይጻፉ።
SGC exists to equip rising Christian leaders around the world by providing free, high-quality theological resources. We gladly grant permission for you to print and distribute our courses under these simple guidelines:
All materials remain the copyrighted property of Shepherds Global Classroom. We simply ask that you honor the integrity of the content and mission.
Questions? Reach out to us anytime at info@shepherdsglobal.org
Total
$21.99By submitting your contact info, you agree to receive occasional email updates about this ministry.
Download audio files for offline listening
No audio files are available for this course yet.
Check back soon or visit our audio courses page.
Share this free course with others