(1) ምን ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም
ይህ የመረጃ እጦት ነው። መሪው መረጃን ማቅረብ አለበት። ሁሉንም የሚፈለገውን ዕውቀት ከሌለው የሚረዳው ሰው መፈለግ አለበት።
(2) እንዴት ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም።
ይህ የስልጠና እጦት ነው። መሪው በድርጅቱ ውስጥ የሚያስፈልጉትን ሁሉንም ክህሎቶች ላይኖሩት ይችላል ነገር ግን ስልጠናን ማዘጋጀት አለበት።
(3) ለምን ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም።
ይህ የመነቃቃት እጦት ነው። አንዳንድ ጊዜ በድርጅት ውስጥ ያሉ ሰዎች የድርጅቱን ግቦች አይረዱም ወይም ተረድተው ነገር ግን ግድ የላቸውም። መሪው ህዝቡ ግቦቹን እንዲጋራ መርዳት አለበት።
(4) ከማድረግ የሚከለክሉአቸው ችግሮች አሉ።
ይህ የመሳሪያ እና የመደራጀት እጦት ነው። መሪው ሰዎች ስኬታማ እንዳይሆኑ የሚያግዷቸውን ችግሮች እንዲፈቱ ሊረዳቸው ይገባል።
ይህ ዝርዝር በድርጅት ውስጥ ያሉ ሰዎች ማድረግ የሚገባቸውን ላለማድረጋቸው አራት የተለመዱ ምክንያቶችን ይሰጣል። እነዚህ አራቱም ምክንያቶች የአመራር ውድቀትን ያሳያሉ።
አንድ መሪ ህዝቡ ማድረግ የሚገባቸውን አላደረጉም ብሎ ሲያማርር መምራት እያቃተው መሆኑን እያወጀ ነው። ለምሳሌ ቤተክርስቲያኑ ወንጌልን አትሰብክም ብሎ የሚያማርር ፓስተር የሚከተሉትን ጥያቄዎች ሊያስብበት ይገባል፦
ወንጌል መስበክ እንዳለባቸው ገልጫለሁን?
ወንጌልን እንዴት እንደሚሰብኩ አስተምሬያቸዋለውን (በተለይም በማሳየት)?
ወንጌልን እንዲሰብኩ አነቃቅቻቸዋለውን?
የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዳይሰጡ የሚከለክሏቸውን ችግሮች እንዲጋፈጡ ረድቻቸዋለውን?
ሁለት ሰራዊቶች በመጠንና እና አንድ አይነት መሳሪያ ካላቸው የትኛው ያሸንፋል። ምርጥ ጀነራል ያለው ሰራዊት ያሸንፋል።
ሁለት የስፖርት ቡድኖች እኩል ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾች አሏቸው። የትኛው ቡድን ያሸንፋል? ምርጥ አሰልጣኝ ያለው ቡድን ያሸንፋል።
የመነቃቃት ፈተናዎች
► እንዲህ የሚል አንድ የድሮ ምሳሌ አለ “ብዕር ከሰይፍ በላይ ሀይል አለው”። ይህ ማለት ምን ይመስልሃል?
በሃሳብ፣ በማሳመን እና በግንኙነት ውስጥ ሃይል አለ ማለት ነው። ሀሳብ ከጦር መሳሪያ የበለጠ ተጽእኖ ይኖረዋል። “ብዕር” በጽሑፍ መግባባትን ያመለክታል ነገር ግን በማንኛውም መልኩ አሳማኝ ግንኙነት ሰዎችን ከፍላጎታቸው ውጪ ከማስገደድ የበለጠ ኃይል አለው።
በአንድ ሰው ሥልጣን ተገደው የሚሰሩ ሰዎች የተቻላቸውን ሁሉ አያደርጉም። ጉልበታቸውን እና ሀሳባቸውን ለሥራው አያውሉም። ሰዎችን ከማስገደድ ይልቅ በማነሳሳት የበለጠ ማከናወን ትችላለህ። አንድ ሀሳብ ወይም ጽንሰ ሐሳብ በሚሊዮኖች ወደ ሚቆጠሩ ሰዎችን ሊሰራጭ እና ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል።
ሁለተኛው የአለም ጦርነት የቃላት ሀይልን የሚያሳይ ምሳሌ ነው። ሁለተኛው የአለም ጦርነት የቃላት ጦርነት፣ የሀሳቦች ጦርነት ነበር።
የቃላት ጦርነት የነበረው ለምንድን ነው? Adolf Hitler ሀይለኛ ተናጋሪ ነበር። ለጀርመን ያለውን ራዕይ አሳወቀ ጀርመኖችም መሪ አደረጉት። ዓለምን መግዛት ያለባቸው ዋና ዘር እነርሱ መሆናቸውን አሳምኗቸዋል። አንዳንድ ቤተክርስቲያናት እንኳ ሳይቀሩ ስለ እርሱ መሲሕነት ይናገሩና ጀርመን የእግዚአብሔር መንግሥት ናት ይሉ ጀመር። Hitler ጀርመንን በታሪክ አስከፊ በሆኑ ድርጊቶች ውስጥ መርቷል። በቃላት ሀይልም ይህንን አድርጓል። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ቃላት ምንም ጉዳት የላቸውም ብለው ያስባሉ ነገር ግን የHitler ቃላት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድለዋል።
Hitler በጀርመን ስልጣኑን እየጨመረ በነበረበት ወቅት በእንግሊዝ የሚኖሩ አንዳንድ ሰዎች ምንም አይነት አደጋ እንደማይደርስባቸው አስበው ነበር። እንግሊዝ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር የምትመርጥበት ጊዜ ሲደርስ አንዳንድ እጩዎች ለህዝቡ ሰላም እንደሚያስገኙ ቃል ገቡ። ነገር ግን Winston Churchill ለህዝቡ እውነትን ተናገረ። እንዲህም አለ “ደም፣ ላብ እና እንባ አቀርባለሁ”። ከችግሮቹ ጋር ስለተጋፈጠ ተመርጧል።
የChurchill ንግግሮች ኢንግላንድ እራሷን ከጀርመን መከላከል እንድትችል አንድ እንዲሆኑ ያደረገ ነበር። እንዲህም አለ “በአየርና በባህር እንዋጋለን። በባህር ዳርቻዎች ላይ ካረፉ በባህር ዳርቻዎች እንዋጋለን። በየትኛውም መንገድ እና ከተማ ውስጥ እንዋጋቸዋለን። መቼም ተስፋ አንቆርጥም። መቼም እጅ አንሰጥም።”
በHitler እና Churchill ንግግሮች የቃላትን ሀይል እንመለከታለን። በአንድ መልኩ እያንዳንዱ ጦርነት የቃላት ጦርነት ነው።
► እያንዳንዱ ጦርነት የቃላት ጦርነት ነው የሚለውን መግለጫ በማብራራት ይግለፁ። ይህ ስለ አመራር ምን ይነግረናል?
አንዳንድ ጊዜ መሪ እርዳታ ማግኘት የሚችለው ለዚያ በመክፈል ብቻ እንደሆነ ያስባል። ብዙ የሚከፍላቸው ከሆነ ህዝቡ የበለጠ እንደሚሰሩ ያስባል። ይህ በአብዛኛው እውነት አይደለም። ሰዎች ድርጅትን የሚረዱሩት ስለሚያምኑበት ነው። ጠንክረው የሚሰሩት የሚጋሩት ግቦች ስላሉ ነው።
ሁሉም ሰው በደንብ የተረዳው የጋራ ግብ ላይ ለመድረስ ካልሰራ በስተቀር ጠቃሚ ስራ ሊኖርዎት አይችልም። ነገር ግን ይህ በቂ አይደለም። ግብ ላይ እንዴት እንደሚደርሱ ማወቅ አስፈላጊ ነው። በእሴቶች መመራት አለብህ። በግቦቹ እና እንዴት እነርሱ ላይ እንደሚደርሱ በሁለቱም መኩራት አለብዎት።[1]
► በግቦቹ እና ግቦቹ ላይ እንዴት እንደሚደርሱ በሁለቱም መኩራት አለብዎት ማለት ምን ማለት ነው?
አንድ የቢዝነስ ሰው ለሰራተኞቹ በመክፈል ብቻ ትልቅ ኩባንያ አይገነባም። በግቦች እና እሴቶች ሊመራቸው ይገባል። ለገንዘብ ብቻ ከሆነ ሰዎች ለቢዝነስ አላማዎች አይሰሩም። ለጥራት ደንታ የላቸውም እና በስራቸው አይኮሩም።
[2] በጣም አስፈላጊ ነገሮች ለገንዘብ አይደረጉም። ሰዎች ለቤተሰቦቻቸው እና ለልጆቻቸው የሚያደርጉትን ነገር አስቡ። በገንዘብ ምክንያት እነዚህን ነገሮች አያደርጉም ነገር ግን በጣም አስፈላጊ ለሆኑ እሴቶች እንጂ፤ ሰዎች በእሴቶቻቸው ይነቃቃሉ።
በአገልግሎት ውስጥ ከንግዱ ዓለም ይልቅ የመሪነት ክህሎት የበለጠ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሠራተኞች በአብዛኛው በጎ ፈቃደኞች ናቸው። መሪው ለአብዛኛዎቹ የሚከፈልበት የሥራ ስምሪት ማበረታቻን መስጠት አይችልም። ቤተክርስቲያንን የሚረዱ ሰዎች ይህን የሚያደርጉት በቤተክርስቲያን ስለሚያምኑ ነው። ቤተክርስቲያን በሀገር ውስጥ በገንዘብ እና በጉልበት ካልተደገፈች የመሪው ውድቀት ነው።
► በቤተክርስቲያናችሁ ውስጥ የሚረዱ ሰዎች እነማን ናቸው? ለምን ያደርጉታል?
የመሪው ሥራ በዚህ መልኩ ተጠቃሏል ፦
ስራው ለምን ጠቃሚ እንደሆነ ሰዎች እንዲያውቁ ያድርጉ። የት እንደሚሄዱ ይወስኑ። ቡድኑ ግቦቹን መጋራቱን ያረጋግጡ። እሴቶችን ለማዘጋጀት እገዛ ያድርጉ። ሀብቶችን ቦታቸው ላይ በማድረግ የፈልጉትን ድጋፍ በድርጅቱ ውስጥ እና ከድርጅት ውጭ እንዳገኙ ያረጋግጡ። ችግርን ለማስወገድ እና አቅጣጫን ለመለወጥ ዝግጁ ለመሆን አይኖትን የወደፊቱ ጊዜ ላይ ያድርጉ።[3]
[1] Ken Blanchard and Sheldon Bowles,
Gung Ho: Turn on the People in Any Organization (New York: William Morrow, 1997), 38
[2]
“በስራ መጠመድ ሁልጊዜ አውነተኛ ስራ እየተሰራ ነው ማለት አይደለም። የሁሉም ስራ አላማ ማምረት ወይም መፈፀም ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ለሁለቱም አላማዎች አስቀድሞ ማሰብ፣ ስርአት፣ እቅድ፣ ብልህነት እና ታማኝ ዓላማ እንዲሁም ላብ መሆን አለበት።”
- Thomas Edison
[3] Ken Blanchard and Sheldon Bowles,
Gung Ho: Turn on the People in Any Organization (New York: William Morrow, 1997), 79
Previous
Next