መግቢያ
አንዳንድ ሰዎች ሁላችንም እኩል በእግዚአብሔር ዘንድ አስፈላጊ ስለሆንን ማንም በቤተክርስቲያን ውስጥ በሌሎች ላይ ስልጣን ሊኖረው እንደማይገባ ያምናሉ። ሌሎች ሰዎች በአመራር እንደሚያምኑ ይናገራሉ ነገር ግን ከማንኛውም መንፈሳዊ ሥልጣን ነፃ እንደሆኑ አድርገው ይንቀሳቀሳሉ።
► መጽሐፍ ቅዱስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሥልጣን መኖር እንዳለበት ያስተምራልን? ምሳሌዎችን አስቀምጥ።
መጽሐፍ ቅዱስ የቤተክርስቲያን አመራርን በብዙ ቦታዎች ይጠቅሳል።[1] (አንዳንዶቹ ምሳሌዎች እኚህ ናቸው ዕብራውያን 13፥7-17፣ ቲቶ 1፥5፣ ሮሜ 12፥8፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥40፣ እና 1ኛ ጢሞቴዎስ 5፥17።)
መሪነትን እንደ ተፅዕኖ መግለፃችን በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን የመሪነት ሚና ለማየት ይረዳናል። አንዳንድ ልዩ ሚናዎች በእግዚአብሔር የተነደፉት መሪዎች ቤተክርስቲያንን ዓላማዋን እንድትፈፅም እንዲረዷት ነው።
► አንድ ተማሪ ለብድኑ ኤፌሶን 4፥11-12 ያንብብ።
[2]ሁሉም የአገልግሎት ሚናዎች በዚህ ዝርዝር ውስጥ በተወሰኑ ጥሪዎች ሊታወቁ አይችሉም። ለምሳሌ፤ ሙዚቀኛ ወይም የአምልኮ መሪ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ላይሆን ይችላል። ሆኖም እያንዳንዱ የአገልግሎት አመራር ሚና ቤተክርስቲያን ዓላማዋን እንድትፈጽም በመርዳት ላይ ማተኮር አለበት።
የመሪነት ሚናዎች በመስበክ፣ በማስተማር እና በስብከተ ወንጌል ብቻ የተገደቡ አይደሉም። የቤተክርስቲያን ሀላፊነት ከዚህም በላይ የሰፋ ነው። የቤተክርስቲያን ሰዎችም ተግባራዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት በጋራ ይሠራሉ። የጓሮ አትክልትን ለማልማት የሚውሉ መሳሪያዎችን በጋራ እንዲጠቀሙ ሰዎችን የሚመራ ሰው ቤተክርስቲያን አባሎቿን የመንከባከብ አላማዋን እንድታሟላ እየረዳት ነው። የቤተክርስቲያን ኃላፊነቶች በቤተክርስቲያኑ ሕንፃ ውስጥ ከሚፈጠረው በላይ አስፈላጊ የሆኑ ብዙ የአመራር ሚናዎችን ያደርጋሉ።
ሥራውን በእኔ በኩል እንዲሠራ በመጠየቅ አበቃሁ።”
- J. Hudson Taylor