የትምህርቱ አላማ
(1) ተማሪው የሚከተሉትን ማስረዳት ይችላል
-
የኃጥያት መነሻ / ምንጭ
-
ስለኃጥያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ቃላትን
-
የተወረሰ ውድቀት ትርጉም እና መግለጫ
-
በፈቃድ የሚሰራ ኀጥያት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሃሳብ
-
ስለ ኃጥያት ክርስቲያናዊ የእምነት መግለጫ
(2) ተማሪዎች በፈቃድ ስለሚሰራ ኀጥያት ጥርት ያለ ትርጉም በመያዝ መለወጥን በሚገባ መረዳት ይችላሉ።
Lesson
Playlist
Search through all lessons and sections in this course
Searching...
No results found
No matches for ""
Try different keywords or check your spelling
1 min read
by Stephen Gibson
(1) ተማሪው የሚከተሉትን ማስረዳት ይችላል
የኃጥያት መነሻ / ምንጭ
ስለኃጥያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ቃላትን
የተወረሰ ውድቀት ትርጉም እና መግለጫ
በፈቃድ የሚሰራ ኀጥያት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሃሳብ
ስለ ኃጥያት ክርስቲያናዊ የእምነት መግለጫ
(2) ተማሪዎች በፈቃድ ስለሚሰራ ኀጥያት ጥርት ያለ ትርጉም በመያዝ መለወጥን በሚገባ መረዳት ይችላሉ።
► ዘፍጥረት 3 አብራችሁ አንብቡ። ይህ ክፍል ኃጢአት ምን ይነግረናል?
► ለምንድን ነው ስለ ኃጥያት መረዳት የሚያስፈልገን?
ኃጥያትን መረዳት ያለብን -
1. የአለምን ሁኔታ ለመረዳት- መጽሐፍ ቅዱስ ኃጥያት የሰው ልጅ መከራ ምንጭ እንደሆነ ይነግረናል። በኃጥያት ምክንያት ሞት ወደ አለም ገባ (ሮሜ 5፥12 ይነበብ)። በኃጥያት እርግማን ውስጥ በሽታ፥ ማርጀት፥ እና ህመም አለ። መዋሸት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ዝሙት፥ ስካር ፥ እና ግፍ የመሳሰሉ ኃጥያት ያለባቸውም ተግባራት ምድር በመከራ ሞሏት። ጥላቻ፥ የአይን አምሮት፥ ቅናት፥ ኩራት እና ራስወዳድነት ከሚመሳስሉ በልብ ውስጥ ካለ ኃጥያት ነው ተግባራቱ የሚመነጩት።
2. ፀጋን እና ድነትን ለመረዳት- እግዚአብሔር ከኃጥያት የሚያድነን ፀጋን ሰጥቶናል (ማቴዎስ 1፥21፤ ሮሜ 5፥20-21)
3. ቅድስናን ለመረዳት- ኃጥያተኝነት የቅድስና ተቃራኒ ነው - ለእግዚአብሔር ያለ መሰጠትም ይቃረናል። እግዚአብሔር በሚጠብቅበት መንገድ ለመቀደስ ሰው ከኃጥያት መራቅ ያስፈልገዋል (1 ጴጥሮስ 1፥15-16)።
እግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ፍፁም ነበር ፤ እርሱ የፈጠረው ሁሉ ያለ ግድፈት ነበር። እግዚአብሔር ፈጥሮ ሲጨርስ፤ ሁሉም መልካም እንደሆነ አየ (ዘፍጥረት 1፥31)፤ በመሆኑም ኃጥያት በእግዚአብሔር ምክንያት የመጣ አይደለም።
አዳም እና ሔዋን ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ነበራቸው፥ እግዚአብሔር ለማስደሰት ይሹ እና ትክክል የሆነውን ሁሉ የማድረግ አቅም ነበራቸው። ሰይጣንም ሔዋን እግዚአብሔር እንዳትታዘዘው ሊያታልላት መጣ፤ በዚህም ኃጥያት በምድር በልዕለ አለሙ ውስጥ እንደነበረ መረዳት እንችላለን። ሰይጣን ቀድሞንን በኃጥያት ወድቋል- ነገር ግን ኃጥያት ወደ ሰው ልጆች እና በሰው ልጆች አስተዳዳሪነት ውስጥ ወዳለው ፍጥረት አልገባም ነበር።
አዳም እና ሔዋን ነፃ ፈቃድ ነበራቸው። ኃጥያት እውን መሆን የቻለው ሰዎች እውነተኛ የሆነ ምርጫ ማድረግ ስለቻሉ ነው። የእግዚአብሔር ህግ መተላለፍን መረጡ፥ ይህም የሰው ልጅ ኃጥያት ጅማሬ ነው።
የመጀመርያው የኃጥያት ተግባር ሰውን ከእግዚአብሔር ለየው፥ ኃጥያትም የሰውን ልጅ ፍጥረት አበላሸው (መዝሙር 51፥5 ይነበብ)። ከዚህ በኃላ የሚወለዱ ልጆች በሙሉ በኃጥያት ህይወታቸው የተበላሸ እና ኃጥያትን የሚያደርጉ ሆኖ (ሮሜ 5፥12፣ 14፣ 18-19 ይነበብ)።
ኃጥያት በፍጥረት ሁሉ ላይ እርግማ አመጣ (ዘፍጥረት 3፥16-19)። ህይወትም ከኃጥያት የተነሳ ተለወጠ- ህመም፥ ማርጀት፥ እና ሞት ጀመሩ (1 ቆሮንቶስ 15፥22 ይነበብ )። ስራ እና ኑሮ ከባድ ሆነ፥ የሰዎች ግንኙነት በግጭት የተሞላ ሆነ፥ አመታት በጨመሩ እና ሰዎች በበዙ ልክ፥ የኃጥያትም መዘዝ አዳም እና ሔዋን ከገመቱት በላይ የበዛ ሆነ።
ብዙ ቋንቋዎች ለኃጥያት የተለያዩ ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ቃላት አሏቸው። የመጀመርያዎች መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈባቸው የዕብራይስጥ እና የግሪክ ቋንቋዎችም፥ ከታች እንደተብራራው፥ በተለያዩ ቃላት ኃጥያትን ለመግለይ እና ለመተርጎም ይጠቀማሉ- እነዚህ ቃላት ስለ ኃጥያት ሙሉ የሆነ ስዕል ይሰጡናል
[1]ኃጥያት እንደ ስልጣንን አለመቀበል- አመፅ (መዝሙር 51፥1) ያዕቆብ ይህንን የዕብራይስጥ ቃል ከላባ ጋር ያደረገው ንዴት በተሞላ ንግግር ውስጥ በእርሱ ላይ የፈፀመው ወንጀል ምን እንደሆነ ሲጠይቅ ይጠቀመዋል (ዘፍጥረት 31፥36)። ይህም ቃል የሞኣብ ንጉስ በንጉስ እዩርብኣም ላይ ፈፀመውን ተግባር ለመግለፅ ጥቅም ላይ ውሏል (2 ነገሥት 3፥7)።
ኃጥያትን እንደ ጠማማነት ወይም መዛባት- የታጠፈ ወይም የተጣመመ (መዝሙር 51፥2a)- ሰይጣን ምንም መፍጠር አይችልም፥ በመሆኑም ኃጥኣት እግዚአብሔር የፈጠረውን መልካም ነገር ሁሉ ማጣመም/ ማዛባት ነው።
ኃጥያት የሚፈለገውን መሳት ወይም ከግብ መጉደል ነው - በመዝሙር 51፥2b ላይ ለኃጥያት ጥቅም ላይ የዋለው ቃል ይህንን ትርጉም ይይዛል። በመሳፍንት 20፥16 ላይም ደግሞ ስለ ስነምግባር ጉድለት ተመሳሳዩ ቃል በገለልተኛ መንገድ ስለ700 ግራኝ የሆኑ ወንጭፍ ወርውረው በአናት ላይ ያለ ፀጉር የማይስቱ ተዋጊዎች ይገልጣል። ኃጥያት እግዚአብሔር ስለ እውነት፥ ቅድስና፥ እና ፅድቅ ያደረውን ምልክት መሳት ነው።
በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያለው ቃል ተመሳሳይ ትርጉም አለው። ቃሉ ለመላው አለም ኃጥያት መጠቀም ይቻላል (ማቴዎስ 1፥21) ፥ ወይም የአንድን ሰው ኃጥያት ለመግለጥ መጠቀም ይቻላል፥ ለምሳሌ የእየሱስን እግር እንዳጠበችው ሴት ኃጥያት (ሉቃስ 7፥48-50) ወይም አንድን ኃጥያት ለመግለጥ ሊሆን ይችላል እንደ እስጢፋኖስ መግደል ኃጥያት (ሐዋርያት ሥራ 7፥60)። ኃጥያት ከእግዚአብሔር ፈቃድ ዞር ማለት ነው።
ኃጥያት እንደ መጥፎ - የመልካም ተቃራኒ (መዝሙር 51፥4)- ይህ ተመሳሳይ ቃል በእብራይስጥ ፈርኦን በህልሙ ያያቸውን ሰባት ከሲታ ላሞችን (ዘፍጥረት 41፥19) እንዲሁም መበላት የማይቻለውን በለስ ኤርምያስ 24፥2 ለመግለጥ ጥቅም ላይ ውሏል።
ኃጥያት እንደ ውድቀት ወይም ለመስማት ፈቃደኛ እንዳለመሆን፥ በንቃት ለሚደረግ አለመታዘዝ ውጤት ነው (ሮሜ 5፥19) - በሐዋርያት ሥራ 7፥57፣ ላይ እስጢፋኖስ ሲወገር ጆሯቸውን የደፈኑ ሰዎችን ባህሪ የሚያመላክት ነው። አለመታዘዝ የሚለው ቃል በግሪክ ያለውን ሃሳብ በሚገባ የሚያስረዳው ቃል ነው።
ኃጥያት የተሰጠን የተወሰነን ህግ መጣስ ነው - እግዚአብሔር ከሚደነግገው በተቃራኒው ማድረግ ነው- (1 ዮሐንስ 3፥4)። ሁለት የግሪክ ቃላት በመጣመር ‘ህግ አልባ’ ወይም “ዐመፅ” የሚል ትርጉም ይሰጡናል።
ኃጥያት አውቆ ከትክክለኛው መንገድ ዞር ማለት ወይም ከሚታወቀው ወይም በእግዚአብሔር ከሚጠብቀው መንገድ አልፎ መሄድ ነው (ዘፀአት 32፥7-8) በዚህ ክፍል ውስጥ ሰዎች ሙሴ ሲና ተራራ ላይ ሆኖ ከእግዚአብሔር መንገድ ዞር ማለት ነው።
ሳናውቅ የሚደረጉ ኃጥያቶች (ዘሌዋውያን 4፥2)- ይህ አይነት ኃጥያት በሁለቱን ብሉይ እና ዐዲስ ኪዳናት ውስጥ ተጠቅሷል። ዕብራውያን 9፥7 ላይ የተጠቀሰው የግሪክ ቃል ‘አላዋዊ መሆን’ ወይም ‘አለመረዳት’ ከሚለው ግስ ሲሆን- ትርጉሙም ‘ኃጥያትን ያለማወቅ ማድረግ’ ፤ ይህም ጥቅስ ሊቀ ካህኑ ባለማወቅ ስለተሰራ ኃጥያት የሚያደርገው የስርየት ስርዓትን የሚገልፅ ነው።
ከእነዚህ ቃላት ውስጥ ኃጥያት ዘርፈ ብዙ የሆነ ችግር እንዳለበት አመላካች ነው። አንዳንድ ቃላት ኃጥያትን በጠቅላላው ሑነቱ የሚገልጡ ሲሆን፤ ሌሎች ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል ባለመስማት ምክንያት ለተቀመጠ ህግ በመጠበቅ መኖር ሲያቅታቸው፥ ሆነ ቀድሞ የታሰበበት ኃጥያት ወይም ባለማወቅ ወይም በስዕተት የሚሰራ ኃጥያት ነው። የትኛውም ኀጥያት ይሁን ግን እየሱስ በመስቀል ላይ ሰዎችን ከኃጥያታቸው ለማዳን እንደሞተ ማወቅ የተባረከ ሃሳብ ነው (ማቴዎስ 1፥21)።
“ኃጥያት እና እግዚአብሔር ልጅ በፍጹም አብረው መሄድ የማይችሉ ናቸው። አንዳንድ ግዜ ይገጣጠማሉ ነገር ግን አብረው በስምምነት መኖር አይችሉም።”
– ጆን ስቶት
► በፈቃድ የሚሰራ ኃጥያት ምንድን ነው?
በፈቃድ የሚሰራ ኃጥያት ማለት ለተገለጠው የእግዚአብሔር ፈቃድን አውቆ መጣስ ነው። (1 ዮሐንስ 3፥4፤ ያዕቆብ 4፥17 ይነበብ)። ሰዎች ስዕተት መሆኑን እያወቁ ማድረግ መቀጠል ወይም ትክክል የሆነውን ነገር ላለማድረግ መምረጥ ነው። አውቆ የሚደረግ የስዕተት ስራ ነው።
በ1 ዮሐንስ 3፥5-6 ላይ ሐዋርያው ዩሐንስ እንዲ ብሎ ይፅፋል
እርሱ እየሱስ ኀጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፤ በርሱም ኀጢአት የለም። በርሱም የሚኖር ኀጢአትን አያደርግም፤ ኀጢአት የሚያደርግ ግን እርሱን አላየውም ወይም አላወቀውም።
በዚህ ክፍል የሚያወራው አውቀን በተደጋጋሚ የሚደረግ ኃጥያት ነው። የዚህ ክፍል ሲብራራ የሚለው ሃሳብ፤ ማንም በክርስቶስ የሚኖር ቢሆን በተደጋጋሚ እና ተለምዶዓዊ ኃጥያት አይሰራም፤ እንዲሁም በተደጋጋሚ እና በተለምዶ ኃጥያትን የሚሰራ ሰው እንዲሁ እየሱስን አላየውም ፥ አያውቀውም።
አንድ ሰው ኃጥያትን በዚህ በጠቅላላው መተርጎም የሚፈልግ ከሆነ (ያለማወቅ ወይም በስዕተት የሚሰራን ኃጥያት ጨምሮ)፥ ይህ አርፍተ ነገር ትርጉም አይሰጠውም። ክርስቲያኖች ከፈቃዳቸው ባለፈ ውድቀት አለባቸው፤ ነገር ግን ማንም ኃጥያት (በዚህ ክፍል ውስጥ እንዳለው) ሲረዳው “የእግዚአብሔርን ህግ በፈቃደኝነት መካድ” በሚል ከሆነ ይህ ክፍል ትክክለኛ ትርጉም ይሰጠናል።
► ሰዎች ይዘውት ስለሚወለዱት ኃጥያተኛ ማንነት ምን ትላላችሁ?
የተወረሰ ውድቀት የሰው ልጅ ከተወለደ ጀምሮ ወደ ኃጢአት እንዲያዘነበል የሚያደርግ የተፈጥሮ ሞራል መበላሸት ነው። አንዳንዴ የሰው የውርስ ኃጥያት ነውም ተብሎ ይጠራል። ይህም በአዳም በሰራው ኃጥያት ምክንያት ያለን ኃጥያተኛ ማንነት ነው።
ሁሉም ሰው ከውልደቱ ጀምሮ ወደ ክፋት ያዘነብላል። (መዝሙር 58፥3 ይነበብ)። የሰው ማንነት ከውልደቱ ጀምሮ ኃጥያተኛ ዝንባሌ ስላለው ከመጀመርያ ፍጥረቱ የተዛባ ኃጥያተኛ ዝንባሌን ሰው ከአካባቢው የሚማረው አይደለም ነገር ግን ምርጫን በራሱ መምረጥ ከሚጀምርበት ግዜ ጀምሮ ከፍጥረቱ ኃጥያትን መስራት ይጀምራል።
ዳዊት ሲናገር በአመፅ ተፀነስኩ፤ በኃጥያትንም ተወለድኩ ብሏል (መዝሙር 51፥5 ይነበብ)። እናቱ ስዕተት ሰርታለች ለማነት ሳይሆን ነገር ግን አንድ ሰው በእናቱ ማዕፀን ውስጥ ገና ሲበጅ ከፍጥረቱ በኃጥያት የተበላሸ ማንነት ይዞ እንደሚሰራ ለማለት ነው።
በተበላሸ ማንነቱ ምክንያት በሰዎች ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር መልክ ተጎድቷል። ሁሉም ሰው ራሱን በሚወድ እና ለኃጥያት በተሰጠ ማንነት ይዞ ይወለዳል (ሮሜ 3፥10-12)። እግዚአብሔር መሻቱን እና ጉልበትን ካልሰጠን በቀር ሰው በራሱ መልካምን የመምረጥ ነፃነት የለውም።(ሮሜ 6፥16-17 ይነበብ።)
የተወረሰ ውድቀት እንደ ኩራት፥ ቅናት፥ ጥላቻ እና ይቅርታ አለማድረድ የመሳሰሉ ነገሮችን እንድንፈልግ ያደርገናል። ኃጥያትያዉ የሆኑ ተግባራትን እንድንመርጥ ያነሳሳናል።
ሰዎች የእግዚአብሔርን ባለስልጣንነት ላይ የሚያምፅ ተፈጥሮዓዊ አመለካከት እና በሰጠው ህግ ላይ ቁጣ አለባቸው። ኃጥያተኞች ስለ ኃጥያተኛ ተግባራቸው ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ስላለው የአመፅ አመለካከታቸውም ይቀጣሉ (ይሁዳ 1፥15 ይነበብ)።
ኃጥያተኛ ማንነት ያለው ሰው በተፈጥሮ ራስ ወዳድ ነው። ለእግዚአብሔር እና ሌሎች ፈቃድ ራሱን ከማስገዛት በላይ ለራሱ ፈቃድ ለመፈፀም የተሰጠ ነው። እግዚአብሔርን ከማስደሰት ይልቅ የራሱን ፍላጎት ለማሟላት የሚፈልግ ነው። በእግዚአብሔር ላይ የሚተማመን ሳይሆን በራሱ የሚተማመን ነው፥ ለእርሱ ዋነው ነገር የራሱ ስኬት እንጂ የእግዚአብሔር ክብር አይደለም።
የሰዎች እውቀት ስለጨለመ ትክክለኛውን ከስዕተቱ በሚገባ መለየት አይችሉም (ኤፌሶን 4፥17-18 ይነበብ)። ሰዎች በተፈጥሯቸው የአለምን አመፀኛ ፈቃድ የሚከተሉ፥ በሰይጣን ቁጥጥር ውስጥ እና በራሳቸውን ኃጥያተኛ ፍላጎት የሚከተሉ በመሆን ራሳቸውን በእግዚአብሔር ቁጣ ስር ያውላሉ (ኤፌሶን 2፥2-3 ይነበብ)። በእያንዳንዱ ደቂቃ የሰዎች ተፈጠሯዊ ዝንባሌ ወደ ኃጥያት ነው (ዘፍጥረት 6፥5)።
ሰዎች የእግዚአብሔር ፀጋ በህይወታቸው የሚያመጣው ለውጥ ካልሆነ በስተቀር መልካም ማድረግ ሆነ መልካምን መሻት አይችሉም። በንሰዓ መመለስ ሆነ እግዚአብሔርን መፈለግ አይችሉም (ዮሐንስ 6፥44 ይነበብ)። በኃጥያታቸው እና በበደላቸው የሞቱ ናቸው (ኤፌሶን 2፥1)። የስነ መለኮት ምሁራን ይህንን ‘ፍጹም ውድቀት’ ይሉታል።
የእግዚአብሔር ፀጋ እንዴት ለሚወረስ ኃጥያት የሚሰጠውን ምላሽ መገንዘብ አስፈላጊ ነው። በመጀመርያ የእግዚአብሔር ኃይል ከወንጌል ጋር አብሮ በመምጣት ለወንጌል ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት እና አቅም ይሰጣል። (ይነበብ ሮሜ 1፥16.) በመቀጠልም የዳነው ሰው ከኃጥያት ቁጥጥር ስር ነፃ ይወጣል (ሮሜ 6፥11-14)፤ ነገር ግን አዲስ የዳነ ሰው ከተወረሰ ኃጥያት ተፅዕኖ ስር መሆኑን ይቀጥላል።
የተወረሰ ኃጥያት ተፅዕኖ በክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ መንገድ ይገለጣል።
1. አዲስ ክርስቲያን በሚፈተን ግዜ በራሱ ፈቃድ ይታገላል
2. አዲስ ክርስቲያን ሊቃወማቸው የሚገቡ የተሳሳቱ መገፋፋቶች ይሰሙታል
3. አዲስ ክርስቲያን ማድረጉን ሳያስተውል የተሳሳተ ምላሽ እና እሳቤ ይኖረዋል
አዲሱ ክርስቲያን ኃጥያት ያለባቸውን ዝንባሌዎች ገና ስላሉት እምነቱን እንዳይተው ሊበረታታ ይገባል። በእግዚአብሔርን መንፈስ የሚመገኘውን ኃይል እና ለውይ ሁል ግዜ መሻት አለበት።
መጋቢው ከአዲሱ ክርስቲያን ጋር ትዕግስት ሊኖረው ያስፈልጋል፤ በሚለው እና በሚያደርጉት ሁሉ ወጥነት አይኖራቸውም እንዲሁም ችግራቸውን ወድያው መለየት አይችሉም።
አንዳንድ ግዜ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ባለማወቅ ወይም በስዕተት ሊያፈርሱ/ ሊጥሱ ይችላሉ፥ በዘሌዋውያን 4፥2-3 ውስጥ አንድ ሰው ይህ አይነት ስዕተት እንደተሳሳተ ባወቀበት ቅፅበት ወድያው መስዋትን ማቅረብ እንዳለበት እንመለከታለን። የክርስቶስ ሞት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ይቀርቡ የነበሩ መስዋቶችን ሁሉ ስለሚተካ፤ ክርስቲያኞች ባለማወቅ ለሚሰሩ ስህተቶች ሁሉ ድነት አላቸው።
[1]መረዳታችን የተወሰነ ስለሆነ ባለማወቅ የሚሰሩ ስህተቶች አይቀሬ ናቸው፤ ለእግዚአብሔር ያልንን ፍቅር ላይ ስለማይጋጩ ከእርሱ ጋር ያልንን ግንኙነት አይነኩብንም። እግዚአብሔር ለእርሱ ያለን ፍጹም ፍቅር እርሱ ከእኛ የሚፈልገውን ሁሉ እንደሚያሟላ ተናግሯል። (ማቴዎስ 22፥37-40፤ ሮሜ 13፥8-10 ይነበብ)፥ ለማናውቀው ነገር ተጠያቂዎች መሆን አንችልም (ያዕቆብ 4፥17 ይነበብ)።
በብርሃን ስንመላለስ (በምናውቀው እውነት ውስጥ ስንመላለስ) ከኃጥያት ሁሉ እንነፃለን (1 ዮሐንስ 1፥7 ይነበብ)። በክርስቶስ የማዳን ስራ ስለምንታመን ባለማወቅ የሰራናቸው ስዕተቶች ከእግዚአብር ጋር ያልንን ግንኙነት ያፈርሱብናል ብለን አንፈራም።
ዘሌዋውያን ባለማወቅ ስዕተት መስራታችንን ስንገነዘብ ንሰሓን እንድንገባ እና እግዚአብሔር ምዕረት እንድንለምን እንዲሁም እግዚአብሔር እንደሚፈልገው ህይወታችንን እንድናስተካክል ያስተምረናል።
የእግዚአብሔርን ቃል ስናጠና፥መንፈስ ቅዱስን ስንከተል፥ ከሌሎች አማኞች ጋር ህብረትን ስናደርግ እና በብስለት ስናድግ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚጣረሰውን ባለማወቅ የምንሰራውን ስዕተት እንቀንሳለን።
► የእግዚአብሔርን ፈቃድ በሚገባ ማወቅ እና ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?
የእግዚአብሔር ፈቃድ የበለጠ ማወቅ እና መከተል የምንፈልግበት ምክንያቶች
1. እግዚአብሔር የሚያሳዝን ምንም ማድረግ ስለማንፈልግ።
2. የትኛውም ስዕተት፥ ባለማወቅም የተሰራ ቢሆንም፥ መጥፎ ውጤት አለው።
3. እንደ ክርስቲያን መልካም ምሳሌ መሆን አለብን።
4. የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስናስወግድ ባለማወቅ በሚሰራ ኃጥያት ጥፋተኛ ነን።
ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ያለን እውቀት ሲጨምር በህይወታችን ያለውን ስዕተቶች ማስተዋል እንጀምራለን። የምናደርገው ነገር ስዕተት መሆኑን ስንገነዘብ ነገር ግን ማድረጋችንን ስንቀጥል፤ ስዕተቱ ባለማወቅ መሆን ያቆማል። መለወጥ ሲያቅተን ስዕተቱ በፍላጎት የሚሰራ ኃጥያት ይሆናል።
አንዳንድ ግዜ የስነመለኮት ምሁራን ኃጥያቶችን በራሳቸው ጎራ አያስቀምጡም፤ ከፍፅምና የጎደለ ነገር ሁሉ ወይም በማወቅ የሚደግ ስዕተት ሁልግዜ ኃጥያት በማለት ይፈርጃሉ። የኃጥያት በራሳቸው ጎራ ስንረዳ የእግዚአብሔር ፀጋ በእኛ ምን መስራት እንደሚፈልግ እንረዳለን።
በፈቃድ የሚሰራ ኃጥያት ሁሉ ሰው ዳግም ሲወለድ ማሸነፍ ይችላል። ዩሐንስ ዳግም የተወለደ ሰው ኃጥያትን መደበኛ ተግባር አያደርግም (1 ዮሐንስ 3፥4-9)። በፈቃድ የሚሰራ ኃጥያት በክርስቶስ ካለን እምነት ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም። በማወቅ የሚደረግ አመፅ የአንድ ክርስቲያን የተለመደ ባህሪ አይደለም።
መቀደስ ሰዎች ፍፁማን ይሆኑ ዘንድ እግዚአብሔር በሰዎች ህይወት ውስጥ ያለውን ኃጥያት ለማጥፋት የሚሰራው ስራ ነው (1 ተሰሎንቄ 5፥23)። የሰዎች ሁሉ መንፈስ፥ ነፍስ እና አካል ሁሉን እንከን አልባ ማድረግ ነው። ቅድስና የሰውን ኃጥያተኛ የሆነ ማንነቱን የሚያሸንፍ ነው።
ያለማወቅ ኃጥያቶች በአላማ የሚደረግ አለመታዘዝ አይደለም፤ ከኃጥያተኛም ማንነት የሚወጣ አይደለም ነገር ግን ከወደቀ አካል እና እውቀት የሚመነጭ ነው። ከዚህ አይነት ኃጥያት ሰው በምድራዊ ህይወቱ መላቀቅ አይችልም። በትንሳኤ ግን የከበሩት ቅዱሳን ሙሉ በሙሉ እና ለዘላለም ( በቋሚነት) ከሁሉም አይነት ኃጥያቶች ነፃ ወጥተዋል።
► የእምነት መግለጫውን ቢያንስ ሁለት ግዜ አብራችሁ አንብቡ።
የሰው ኃጥያት ከሚመነጨው በመጀመርያ የተፈጠሩት ሰዎች እግዚአብሔር ካለመታዘዛቸው ነው። ሑሉም ሰው፤ ከእየሱስ ክርስቶስ በስተቀር፥ ከአዳም የተወረሰ ውድቀት እና የኃጥያት ተግባራት ጥፋተኝነት አለበት። የሰው ስዕተቶች የእግዚአብሔርን ህግ ሊጥሱ ይችላሉ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት አያፈርስብንም። ሁሉም ኃጥያተኛ ከመጨረሻው ፍርድ በፊት ከእግዚአብሔር ምዕረትን ካላገኘ ለዘላለም የተፈረደበት ይሆናል።
(1) የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የቤት ስራ፦ ከታች ከተዘረዘሩት ዘርፎች መካከል እያንዳንዱን ተማሪ አንድ ይመደብ። ከሚቀጥለው ክፍለ ግዜ በፊት ክፍሉን አንብባችሁ በትምህርቱ ውስጥ ካለው ሃሳብ ላይ ምን እንደሚናገር በአንድ አንቀፅ ፃፉ።
ሮሜ 1፥21-32
ሮሜ 3፥10-20
ገላትያ 5፥16-21
ኤፌሶን 5፥1-8
ቲቶ 1፥10-16
ያዕቆብ 4፥1-4
2 ጴጥሮስ 2፥9-17
(2) ፈተና፦ የሚቀጥለው ክፍለ ግዜ የምትጀምሩት በትምህርት 5 ፈተና ነው። ለፈተና ዝግጅት እንዲሆን የፈተና ጥያቄዎችን አጥኑ።
(3) የማስተማር የቤት ስራ፦ ከክፍል ውጪ የማስተማርያ ግዜን ቀጠሮ መያዝ እና ማስተማራችሁን ሪፖርት ማድረግ አስታውሱ።
(1) ኃጥያትን መረዳት ያልብን ሦስት ዋና ምክንያቶች ዘርዝሩ።
(2) ኃጥያት በእግዚአብሔር ምክንያት የሖነ እንዳልሆነ በምን እናውቃለን?
(3) ለሚከተሉት ለእያንዳንዱ በአንድ አርፍተ ነገር ትርጉም ጻፉ፤ በፈቃድ የሚሰራ ኃጥያት፥ የተወረሰ ውድቀት፥ ባለማወቅ የሚሰሩ ስህተቶች።
(4) የእግዚአብሔርን ፈቃድ አብዝተን መፈለግ እና ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?
15 lessons · አማርኛ
Your print request has been recorded. Your download should begin shortly.
Download Print-Ready FileFree to print for ministry use. No changes to content, no profit sales.
SGC exists to equip rising Christian leaders around the world by providing free, high-quality theological resources. We gladly grant permission for you to print and distribute our courses under these simple guidelines:
All materials remain the copyrighted property of Shepherds Global Classroom.
Questions? info@shepherdsglobal.org
Total
$21.99Added to Cart!
By submitting your contact info, you agree to receive occasional email updates about this ministry.
Download audio files for offline listening
No audio files are available for this course yet.
Check back soon or visit our audio courses page.
Share this free course with others