Type at least 2 characters to search
No results found for ""
Courses
Lessons
navigate open
See all results →

Lesson

Playlist

ክርስቲያናዊ እምነት

ክርስቲያናዊ እምነት

Search Course

Type at least 3 characters to search

Search through all lessons and sections in this course

Searching...

No results found

No matches for ""

Try different keywords or check your spelling

results found

ክርስቲያናዊ እምነት

Lead Writer: Stephen Gibson

Course Description

ይህ ትምህርት መሰረታዊ የሆኖ በክርስትና ስነመለኮት ምድብ ውስጥ እንደ እግዚአብሔር፥ ክርስቶስ፥ ሀጥያት ፥ ድነት እና ሌሎች ዋና አስተምሮዎችን ያስረዳል። ተማሪዎች በአስተምሮ ላይ ያሉ ስዕተቶችን ማስወገድን ይማራሉ። ተማሪዎቸ ሌሎችን ስለ ክርስቲያናዊ አስተምሮ ሌሎችን ለማስተማር ብቁ ይሆናሉ።

What You'll Learn

የእግዚአብሔር መጽሐፍ
የእግዚአብሔር ባህሪያት
ሥላሴ
ሰው
ኃጥያት
መናፍስት
ክርስቶስ
ድነት
በድነት ዙርያ ያሉ ጉዳዮች
መንፈስ ቅዱስ
ክርስትናዊ ቅድስና
ቤተክርስቲያን
ዘላለማዊ እጣ
የመጨረሻ ሑነቶች
ጥንታዊ የእምነት መግለጫዎች

Course Objectives

(1) የክርስትና እምነት መሰረታዊ አስተምሮዎችን መማር

(2) መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ እንደ አስተምሮ ምንጭ እና ባለስልጣን በሚገባ ይጠቀማሉ

(3) በአስተምሮ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና ስዕተቶችን ያለያሉ

(4) ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጣናከር የሚረዳ መረዳትን ይገበያሉ

(5) ሌሎችን ለማስተማር የሚረዳ ይዘት እና ቅርፅ ያገኛሉ

Introduction

ለክፍል መሪዎች የሚሆን መምሪያ

እያንዳንዱ ትምህርት 90 ደቂቃ እንደሚወስድ እንገምታለን። ትምህርቶቹ በሁለት ክፍለ ግዜ ለቡድኑ መስጠት የተሻለ ነው። ቡድኑ ሁለት ግዜ ቢገናኝ፥ አንዳንድ መምሪዎች ሊስተካከሉ ይገባል። ለምሳሌ ሁለቱም ግዜ ፈተና መሰጠት የለበትም።

እያንዳንዱ ተማሪ ይህ መጽሐፍ በእጁ ላይ ሊኖር ይገባል።

ለክፍል መሪዎች የሚሆኑ ማስታወሻዎች ስለ ትምህርቶቹ የተወሰኑ ክፍሎች መመሪያዎችን በመያዝ በመላው ኮርሱ ውስጥ ተካተዋል።. እነሱ በኢታሊክ ተጻፈዋል።

በከፍለ ግዜው መጀመርያ ላይ - ያለፈውን ትምህርት መሰረት ፈተና ስጡ። እያንዳንዱ ተማሪ ያለምንም እርዳታ ፈተናውን መመለስ ያለበት የተማረውን በማስታወስ መሆን አለበት። ተማሪው ፈተናውን ማለፍ ካልቻለ፥ ሌላ ግዜ እንዲፈተን ዕድል መስጠት (በግምት የሚሰጥ ግዜ - 10 ደቂቃ)። የፈተና መልስ ቁልፍ ከ ShepherdsGlobal.org ማውረድ ይቻላል።

ከፈተናው በሓላ፥ ካለፈው ትምህርት አላማ ዝርዝር እንደ ማጥኛ ጥያቄዎች ተጠቀሙ። ከእያንዳንዱ አላማ ጥያቄ ተማሪዎችን በመጠየቅ ተማሪዎች እንዲያስረዱ ፍቀዱ (በግምት የሚሰጥ ግዜ ፤ 15 ደቂቃ)።

አዲስ ትምህርት የተሰጠውን ክፍል በማንበብ ጀመሩ፤ ተማሪዎችም ስለ ትምህርቱ ይዘት ክፍሉ የሚናገረውን እንዲወያዩ አድርጉ (በግምት የሚሰጥ ግዜ- 10 ደቂቃ)

ትምህርቱ ማስተማርያ መፀሐፍ ውስጥ እያንዳንዱን ክፍል በማንበብ እና በማስረዳት ተመልከቱ። የክፍሉ አባላት አንዳንድ ዘርፎችን ማስተማር ይችላሉ ( በግምት የሚሰጥ ግዜ- 45 ደቂቃ)

በዚህ ትምህርት ውስጥ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘርፎች ጥቅም ላይ ውለዋል። የመጽሐፍ ቅዱስ ዘርፎች ማጣቀሻ በቅንፍ ውስጥ አንብብ ከሚለው ጋር ያሉት በክፍል ውስጥ ጮክ ተብሎ መነበብ አለበት። ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ዘርፎች ግን በማስተማርያው መጽሐፍ ውስጥ ያለውን ላለው ሃሳብ ድጋርፍ ሚሰጡ ናቸው። ሁል ግዜ በክፍል ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎቸን መመልከት እና ማንበብ አስፈላጊ አይደለም።

የውይይት ጥያቄዎች እና የክፍል ውስጥ እንቅስቃሴዎች ► በዚህ ምልክት ይለያሉ። አንዳዴ የውይይት ጥያቄዎች የትምህርቱን ክፍል ያስተዋውቃሉ፤ ሌላ ግዜ በክፍል ውስጥ የነበረውን ትምህርት ይከልሳሉ። የክፍሉ መሪ ጥያቄዎችን መጠየቅ አለበት እና ለተማሪዎችም መልሱ ላይ እንዲወያዩ ግዜ መስጠት አለበት። በዚህ ግዜ መልሱን ሙሉ ለሙሉ ማስረዳት አስፈላጊ አይደለም፥ በተለይ ጥያቄው ለክፍለ ግዜው መግቢያ ከሆነ።

በክፍለ ግዜው መጨረሻ ላይ ሙሉ ክፍሉ አብሮ ሁለት ጊዜ ‘የእምነት መግለጫውን’ ያንብብ።

በእያንዳንዱ ትምህርት መጨረሻ ላይ- እያንዳንዱ ተማሪ ከተዘረዘሩት መካከል አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይመደባል። ከሚቀጥለውን ክፍለ ግዜ በፊት፤ ክፍሉን አንብቦ እና አንድ አንቀፅ ክፍሉ ስለ ትምህርቱ ርዕሰ ጉዳይ ስለሚናገረው ይፃፍ። የፃፉትንም አንቀፅ ለክፍሉ መሪ በሚቀጥለው ክፍለ ግዜ ያሳዩ።

ቢያንስ ለሶስት ግዜ ተማሪው ይህንን ትምህርት ወይም የትምህርቱን አንድ ክፈል በክፍል ውስጥ ለሌሉ ሰዎች ያስተምር። ይህም በቤተክርስቲያን ውስጥ ላለ ክፍል፥ ለቤት ለቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን ወይም ሌላ ስብስብ ውስጥ መሆን ይችላል። በእያንዳንዱ ክፍለ ግዜ ማለቂያ ላይ ተማሪዎችን ስለ ቤት ስራ ማስታወስ እንዲሁም ካለፈው የትምህርት ግዜ በሓላ ያስተማሩት ቡድን ካለ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጠይቁ።

በክፍለ ግዜው መጨረሻ ላይ ቀጣዩን ትምህርት ከሚቀጥለውን ክፍለ ግዜ በፊት አንብበው እንሚመጡ አስታውሷቸው (ለማሳሰቢያ እና ለቤት ስራ የሚያስፈልገው ግዜ በግምት - 10 ደቂቃ)

ተማሪዎች ክፍለ ግዜውን የመሳተፍ እና የቤት ስራቸውን በግዜ የመስራት ግዴታ አለባቸው። ተማሪ ክፍል ከቀረ፥ ያለፈውን ትምህርት ማጥናት፥ ፈተናውን መስራት እና የቤት ስራውን መፈፀም አለበት። በትምህርቱ መጨረሻ ላይ የተሰጡ እና የተጠናቀቁ የቤት ስራዎችን መመዝገቢያ ቅፅ አለ።

ለተማሪዎች መምሪያ

ለትምህርት ወደ ክፍል ከመምጣታችሁ በፊት በውይይቱ ላይ በተሻለ ግንዛቤ መሳተፍ እንድትችሉ የተሰጠውን መማርያ አንብባችሁ መምጣት አለባችሁ።

በእያንዳንዱ ክፍለ ግዜ መጀመርያ ላይ ያለፈውን ትምህርት መሰረት ፈተና ስለሚኖር በተሰጠው የማጥኛ ጥያቄዎች መሰረት ተዘጋጁ።

ወደ ክፍል ስትመጡ መጽሐፍ ቅዱስ፥ በታተመ የትምህርቱን ቅጂ እና የራሳችሁን ማስታወሻ መጨመር የሚያስችላችሁ እስኪብርቶ ይዛችሁ ወደ ክፍል መምጣት አለባችሁ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎትን ለማጣቀስ፥ የውይይት ጥያቄዎችን ለመመለስ እና የክፍሉ መሪ በሚመራው መንገድ ለመሳተፍ ተዘጋጅታችሁ መምጣት አለባችሁ።

በእያንዳንዱ ትምህርት መጨረሻ ላይ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይመደብላችሃል፤ ከሚቀጥለውን ክፍለ ግዜ በፊት ክፍሉን አንብባችሁ፤ በአንድ አንቀፅ ስለ ትምህርቱ ዋና ሃሳብ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሉ የሚለውን በማስቀመጥ፤ ለክፍሉ መሪ ማሳየት።

ትምህርቱ በሚሰጥበት ወቅት ቢያንስ ሶስት ግዜ የተማሩትን ትምህርት ወይምን የተመረጠ ክፍል በመውሰድ በክፍሉ ውስጥ ለሌሉ ሰዎች ማስተማር አለባቹ። ይህንም የማስተማር ሀላፊነት በቤተክርስቲያን ውስጥ ላለ ክፍል፥ የቤት ለቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን ወይን በሌላ መንገድ ሊሆን ይችላል። ባስተማራችሁ ግዜ ሁሉ ለክፍል መሪያችሁ አስታውቁ።

Ready to Start Learning?

Choose a lesson to begin your journey through this course.