የትምህርት ዓላማዎች
በዚህ ትምህርት መጨረሻ ተማሪው የሚከተሉትን ማድረግ ይኖርበታል፦
(1) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሥራ ምን እንደሚያስተምር ማብራራት።
(2) የክርስቲያን የሥራ ሥነ ምግባር ባህሪያትን ማሳየት።
Lesson
Playlist
Search through all lessons and sections in this course
Searching...
No results found
No matches for ""
Try different keywords or check your spelling
1 min read
by Stephen Gibson
በዚህ ትምህርት መጨረሻ ተማሪው የሚከተሉትን ማድረግ ይኖርበታል፦
(1) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሥራ ምን እንደሚያስተምር ማብራራት።
(2) የክርስቲያን የሥራ ሥነ ምግባር ባህሪያትን ማሳየት።
ወንድም Lawrence በ1600ዎቹ ውስጥ በአንድ ገዳም ውስጥ የኖረ ተራ መነኩሴ ነበር። ድንች በመላጥ እና የምግብ ሰሀን በማጠብ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተነሣ እና የእግዚአብሔር መገኘት ከአእምሮው እንዲርቅ ባለመፍቀድ በጣም የተለመደ ሥራ በመሥራት ዝነኛ ሆነ። እርሱ ሥራውን ጨምሮ በሕይወቱ በሙሉ እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ ማዕከላዊ ትኩረቱ አደረገው።
The Practice of the Presence of God (የእግዚአብሔር መገኘት ልምምድ) በሚሊዮኖች የተነበበ በጣም ግልፅ መጽሐፍ ነው። የወንድም Lawrence ቃለ መጠይቆችን እና ፅሁፎችን ይዟል። እርሱ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “መቀደሳችን የተመካው ሥራችንን በመለወጥ ላይ አይደለም፣ ነገር ግን በተለምዶ የምናደርገውን ሥራ በማድረግ፣ ለራሳችን ጥቅም ሳይሆን ለእግዚአብሔር ክብር ነው።”
► ሥራ ምንድን ነው? ሥራ መቀጠር ብቻ ነውን አንድን ነገር ለመሥራት መቀጠር?
ሥራ መቀጠርን ያጠቃልላል ነገር ግን እራሳችንን እና ሌሎችን መንከባከብን፣ ያለንን ነገር ማስተዳደርን፣ ነገሮችን ማምረትን፣ ንግድን ለትርፍ መስራት እና ሌሎችን በነፃ መርዳትን ያካትታል።
► አማኝ መሥራት አለበት? ለምን?
ብዙ ሰዎች በቂ ገንዘብ ማግኘት በጣም ጥሩ እንደሆነ ያስባሉ ይህም ስራ ላለመስራት ነው። በጣም አስደሳች ሕይወት የድሎት ህይወት ነው ብለው ያስባሉ።
እግዚአብሔር በመጀመሪያ ዓለምን እንዴት እንደሠራ አስብ። ፍጹም ነበር (ዘፍጥረት 1፥31)። እግዚአብሔር ለፈጠራቸው ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች ፍጹም የሆነ አካባቢ ነበር። እግዚአብሔር ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች ሥራ ሰጣቸው (ዘፍጥረት 1፥28)። እግዚአብሔር ዓለምን ያለ ሥራ ሁሉንም የሰው ልጆች ፍላጎቶች እንዲያሟላ ሊፈጥር ይችል ነበር ግን አላደረገም። እግዚአብሔር ለሰዎች የተሻለው ሕይወት ሥራን እንደሚጨምር ያውቃል።
እግዚአብሔር ሥራችን ከግንኙነታችን ጋር እንዲያያዝ አቀደ። ሰዎች መተባበርን መማር አለባቸው፣ እርስ በርሳቸው ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ፣ እርስ በርሳቸው እንዲተማመኑ፣ ጥንካሬዎችን መጠቀም እና የሌሎች ድክመቶችን መርዳት፣ ችግሮችን በጋራ መቋቋም፣ አለመግባባቶችን መፍታት፣ ስህተቶችን ማረም፣ መሰልጠን እና ሌሎችን ማሰልጠን።
እግዚአብሔር ምድርን እንዲያስተዳድሩ፣ እንዲቆጣጠሩት እና ለክብሩ እንዲያሳድጓት ለሰዎች ሥልጣንና ኃላፊነት ሰጣቸው። ይህ ተግባር ለእርሻ ልማት፣ ለእንስሳት እርባታ፣ ከምድር ላይ ማዕድን ማውጣት እና የቴክኖሎጂ እድገት እንዲኖር አድርጓል።
እግዚአብሄር ከፍጥረት በላይ እንድንሆን አርጎ የፈጠረን በውስጣችን የእርሱ ተፈጥሮ ስላለን ነው። መዝሙረ ዳዊት 8፥6-8 ይላል።
በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ [የሰው ልጅ ማለት ነው] ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤ በጎችንና ላሞችን ሁሉ፣ የዱር አራዊትንም፣ የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሦችን፣ በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትንም ሁሉ አስገዛህለት።
በመጀመሪያው ኃጢአት ምክንያት ዓለም ተለወጠ እና ሥራ በእግዚአብሔር የመጀመሪያ ንድፍ ውስጥ ያልነበሩ ብዙ ችግሮችን እና ቁጣን ያካተተ ሆነ (ዘፍጥረት 2፥17-19)። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ሥራ እንድንፈልግ እንደፈጠረን መገንዘብ አለብን።
የእኛ ሥራ ከእግዚአብሔር የፍጥረት ሥራ ጋር ተመሳሳይ ነው። ሥራ የሰው ልጅ አካባቢውን የሚቀይርበት መንገድ ነው። ገቢ ማግኘት የስራ አላማ ብቻ አይደለም። ሰዎች አካባቢያቸውን የመለወጥ ፍላጎት አላቸው። ቤታቸውን ለማሻሻል ይሞክራሉ። ቆሻሻን ለማስወገድ ይሞክራሉ። መስራት የማይፈልግ ሰው አካባቢውን የመለወጥ ፍላጎቱን እና አቅሙን ትቷል። ሰው የመሆንን ትርጉም አንድ ክፍል እየተወ ነው።
► በደንብ ያልተጠበቀ ቤት ወይም ግቢ ሲያዩ ምን ያስባሉ?
የሰው ልጅ የመፍጠር፣ የማቀድ፣ የማደራጀት እና የማፍራት አቅጣጫ ስራ በሰው ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር መልክ አካል ነው። ስለዚህ ሥራ ሁሉ ለአማኙ የተቀደሰ ነው። ሥራ ሁሉ ጌታን ለማስደሰት ሲደረግ የአምልኮ ተግባር ነው (ቆላስይስ 3፥17፣23)። ኢየሱስ አባቱ እንደሰራ ተናግሯል፣ ስለዚህም እርሱ እንዲሁ ሰርቷል (ዮሐንስ 5፥17)።
ሥራን እንደ አንድ ደስ የማይል አስፈላጊነት የሌለው ነገር ማሰብ የለብዎትም፣ ለምሳሌ በሚታመሙበት ጊዜ መድሃኒት እንደ መውሰድ። ሥራ ለህልውና አስፈላጊው ነገር ብቻ አይደለም። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠው ንድፍ አካል ነው።
2ኛ ተሰሎንቄ 3፥10 መስራት አለብን ይላል “ከእናንተ ጋራ በነበርንበት ጊዜ፣ “ሊሠራ የማይወድድ አይብላ” ብለን ይህን ትእዛዝ ሰጥተናችሁ ነበርና”።
ስራችን አላስፈላጊ እንደሆነ ከመሰለ ምን እናድርግ? Mahatma Gandhi “የምትሰራው ነገር እዚህ ግባ የማይባል ሊመስል ይችላል፣ ነገር ግን ማድረግህ በጣም አስፈላጊ ነው ብሏል።” ወለል ለመጥረግ የተቀጠረ ሰው በዓይነ ሕሊናህ ይታይህ። ይህ ሥራ እዚህ ግባ የማይባል ሊመስል ይችላል ነገርግን አንድ አስፈላጊ ምርጫ እያደረገ ነው። በየቀኑ ወደ ሥራ ሲሄድ ለማንም ምንም ዋጋ ሳይሰጥ ጊዜውን በከንቱ ከማሳለፍ ይልቅ ያንን ለማድረግ እየመረጠ ነው። በጓደኛ ወይም በቤተሰብ ላይ ጥገኛ ከመሆን ይልቅ ራሱን የመርዳት ኃላፊነት መውሰድን እየመረጠ ነው። እርዳታ እንዲፈልጉ ከማስገደድ ይልቅ በእርሱ ላይ ጥገኛ የሆኑትን ምናልባትም ሚስትና ልጆችን ይንከባከባል። እነዚህ ሁሉ አስተያየቶች ሥራው ራሱ እዚህ ግባ የማይባል ቢመስልም እርሱን ለመሥራት መምረጡ አስፈላጊ መሆኑን እንድንገነዘብ ይረዱናል።
በእውነት መሥራት የማይችሉ ብዙ ሰዎች አሉ? በፍጹም። አንድ ሰው ለደሞዝ ተቀጥሮ መሥራት ባይችልም እንኳ የሌሎችን ፍላጎት ለማሟላት የሚረዳ አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል።
የክርስቶስ ተከታዮች ለራሳቸው እና ለሌሎች ተጠያቂዎች ስለሆኑ መስራት አለባቸው። የሚችሉትን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ሌሎች የሚያስፈልጋቸውን እንዲያሟላላቸው መጠበቅ የለባቸውም።
አማኝ በመጀመሪያ ለቤተሰቡ ተጠያቂ ነው። “አንድ ሰው ዘመዶቹን፣ በተለይም የቅርብ ቤተ ሰቡን የማይረዳ ከሆነ ሃይማኖቱን የካደ፣ ከማያምንም ሰው ይልቅ የባሰ ክፉ ነው” (1ኛ ጢሞቴዎስ 5፥8)።
አማኝ የሌሎችን ፍላጎት ለማሟላት እንዲሰራ በመፅሐፍ ቅዱስ ታዝዟል። “ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ለተቸገሩት የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በገዛ እጆቹ በጎ የሆነውን እየሠራ ለማግኘት ይድከም” (ኤፌሶን 4፥28)። አንድን ነገር በከንቱ በመውሰድ በሚሰርቅ ሰው እና እንዲሰጥም በሚሰራ መካከል ያለውን ልዩነት አስተውል። አማኝ የማይሰርቅ ብቻ ሳይሆን ለመስጠት የሚሰራ ነው።
በማንም ባትቀጠርም የምትሰራውን ስራ ልታገኝ ትችላለህ። አጋዥ ለመሆን እና የሌሎችን ፍላጎት ለማሟላት መንገዶችን ይፈልጉ። ምንም ነገር ከማድረግ እና ማንም አልረዳኝም ብሎ ከማማረር በዚያ መንገድ መኖር ይሻላል።
አማኞች እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ለመርዳት እና ለሌሎች ፍላጎት ላላቸው ሰዎች መስጠት እንዲችሉ መስራት አለባቸው።
► ፍላጎቱን ሊያሟላ በእግዚአብሔር ላይ ስለሚደገፍ እና እኔ አልሰራም ለሚል ሰው ምን ትላለህ?
እስኪ ያስብት አንድ በጋ መገባደጃ ላይ ወደ ጓሮዎ ሲሄዱ በመሬቱ አንድ ትልቅ ክፍል ቲማቲም፣ በቆሎ፣ ባቄላ እና ሌሎች አትክልቶችን አብቅሏል። እርስዎን ለረጅም ጊዜ የሚያቆይ በቂ ነበር።
ይህ ተአምር ይመስላልን? ባለፈው ክረምት በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ተከስቷል። ወደ ጓሮቻቸው ገቡ እና ይህ ሁሉ እያደገ እና የበለጠም አገኙ። ነገር ግን አልተገረሙም እንዲያውም አልተደነቁም ምክንያቱም ከጥቂት ወራት በፊት መሬቱን በማልማት፣ ከዚያም ዘሮችን በመትከል፣ ከዚያም ለወራት ውሃ መጠጣቱን እና አረም መታረሙን አረጋግጠዋል። ስለዚህ ሰብል ሲያበቅል ይህ ሲጠባበቁት የነበረ ነገር ብቻ ነበር።
“ከዚያ ይህ በጭራሽ ተአምር አልነበረም” ብለው ምላሽ ሊሰጡ ይችላሉ። እግዚአብሔር ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ እፅዋትን ፈጠረ እና ሰዎች አንድም ጊዜ አልፈጠሩም። መዝሙረ ዳዊት 104:14 እንዲህ ይላል፣ “ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ ለእንስሳት ሣርን፣ ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ”። እግዚአብሔር ያደርገዋል ነገር ግን ሰዎች መሬቱን በማዘጋጀት፣ ዘር በመትከል እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ውሃ በማጠጣት ያዘጋጃሉ።
ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ድርጊት እንደ ኢየሱስ ሲፈውስ ወይም ፀሐይ ፀንታ መቆም ያለውን ከተፈጥሮ ሕግ የተለየ ነገር አድርገው ያስባሉ። ስለዚህ ከዚህ አንጻር የእጽዋት እድገት ተአምራዊ አይደለም ምክንያቱም ተራ ነው።
ነገር ግን ተአምርን በመመኘት ብዙውን ጊዜ የእግዚአብሔርን የተለመደ የነገሮችን አሠራር ችላ እንላለን። ዛሬ ወደ ጓሮአቸው የገቡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ነበሩ እና የሚበሉትን ምንም የሚያድግ ነገር አላገኙም። የእግዚአብሔርን ምግብ የማምረት መንገድ አልተካፈሉም። የምግብ እድገት ሂደት የእግዚአብሔር መደበኛ የስራ መንገድ አንድ ምሳሌ ነው። ለምሳሌ፣ የእግዚአብሔር የተለመደ የፍላጎት አቅርቦት በሰው ሥራ ነው። ምሳሌ 14፥23 ይህን ያስተምረናል “ለፍተው የፈለጉት ትርፍ ያስገኛል፣” ምሳሌ 19፥15 “ዋልጌም ሰው ይራባል” ሲል ያስጠነቅቀናል።
እግዚአብሔር አንድ ነገር እንዲሰጣቸው የሚፈልጉ ሰዎች አሉ ነገር ግን የመሥራት እድሎችን አይቀበሉም ምክንያቱም እነዚህ እድሎች ማድረግ የሚፈልጓቸው ነገሮች አይደሉም።
ለመስራት ፈቃደኛ ከሆናችሁ ግን የሚቀጥርዎት ሰው ካላገኙስ? ሌሎችን ለመርዳት ልታደርጉት የምትችሉት ሥራ አለ እና በዚህ ስራ አንዳንድ ፍላጎቶችዎን ማሟላት ይችላሉ። ሥራ ፈት ከሆንክ ጊዜ አለህ። ለምን ዘወር ብለህ አትመለከትም እና ሌላ ሰው ለመርዳት ምን ማድረግ እንደምትችል አትመለከትም?
እስቲ ሥራ አጥ ሆኖ በየቀኑ ረጅም ሰዓት ተቀምጦ ምንም ሳያደርግ የሚያጠፋ አንድ ሰው አስብ። በእርግጥ ለእርሱ ያደረገው ዘንድ ምንም ዋጋ ያለው ነገር የለምን? በእርሱ አካባቢ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። በጓሮው ውስጥ እና በመንገድ ላይ መፀዳት ያለበት ቆሻሻ አለ። ምግብ ለማምረት ሊለማ የሚችል መሬት አለ። ለማንበብ እና እውቀቱን ለመጨመር የሚያስችል መጽሃፍቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ሊፀልይለት የሚችለው ሰው አለ። ተቀምጦ ምንም የማይሰራ ሰው አንድ ሰራተኛ አለው እርሱ ራሱ እና ሰራተኛው አያመርትም ወይም አያዳብርም። እርሱ ለራሱ ጥሩ ቀጣሪ ስላልሆነ ሌሎችን የማስተዳደር እድል ላያገኝ ይችላል።
በብዙ ጊዜያት እና ቦታዎች ብዙ ሰዎች በአንድ ሰው አይቀጠሩም። የሚለዋወጡትን ነገር ያመርታሉ ወይም ለሌሎች አገልግሎት ይሰጣሉ። እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠን መንገዶች ናቸው።
የኃላፊነት እና የታማኝነት መርሆዎች አማኞች በስራቸው ላይ እንዲተገበሩ አንዳንድ ስነ-ምግባርን ይሰጣሉ።
► አንድ አማኝ ለቀጣሪ ሲሠራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎችን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል?
አዲስ ኪዳን ለሠራተኞች መመሪያ ይሰጣል። የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በተጻፉበት ጊዜ ብዙ ሠራተኞች ባሪያዎች ነበሩ። በዛሬው ጊዜ አንድ ሠራተኛ ከባሪያው የሚለየው ወደ ተለያየ ሥራ የመግባት ዕድል ስላለው ነው። ይህ ነፃነት የቅጥር ውልን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ያስችላቸዋል። ነገር ግን ለተወሰኑ ጥቅማጥቅሞች ለመሥራት ከተስማሙ ከአሠሪው ጋር እስካሉ ድረስ ጥሩ ሠራተኞች እንዲሆኑ በመፅሐፍ ቅዱስ ይጠበቅባቸዋል።
መስራት የምትፈልገውን ስራ ለመምረጥ ነጻ በማትሆንበት ሁኔታ ውስጥ ልትሆን ትችላለህ። ምናልባት ጨቋኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ለመሥራት ትገደዳለህ። አሁንም የክርስቶስ አመለካከት ሊኖርህ ይገባል። አንዳንድ ሰዎች ሲገደዱ በቀስታ እና በመጥፎ ይሰራሉ ምክንያቱም ለመስራት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ለማሳየት ይፈልጋሉ። አንድ ሰው ይህን ሲያደርግ ነፃ እንዳልሆነ ያሳያል። በነጻነት መስራት ከፈለግህ በደስታ መስራት እና ስራውን በጥሩ ሁኔታ መስራት አለብህ። እንደዛ ስትሰራ በነጻነት እየሰራህ ነው፣ ምክንያቱም ያንን እንድታደርግ ማንም ሊያስገድድህ አይችልም።
ማንም ካልቀጠርዎት እርስዎ የራስዎ ተቆጣጣሪ ነዎት። ለራስህ ምን አይነት ሰራተኛ ነበርክ?
ኤፌሶን 6፥5-8 - የኃላፊነት መርህ
► አንድ ተማሪ ለብድኑ ኤፌሶን 6፥5-8ን ያንብብ። የዚህን ምንባብ ትርጉም ተወያዩበት፣ ከዚያም ወደ ምልከታዎ ለመጨመር ከታች ያለውን ዝርዝር ይመልከቱ።
አንዳንድ የኤፌሶን 6፥5-8 ማመልከቻዎች
1. ሠራተኛ ለአሠሪው መታዘዝ አለበት አሰሪው ሲመለከት ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ ነው። ይህ ማለት ደግሞ ሊመረመሩ እንደማይችሉ የሚያውቀውን ዝርዝር ነገር ችላ ማለት የለበትም (“...ለታይታና ከእነርሱ ሙገሳን ለማግኘት ሳይሆን....”)።
2. ሠራተኛ ለእግዚአብሔር እንደሚሠራ ያህል የሥራውን ጥራትና ትጋት መጠበቅ ይኖርበታል (“...እንደ ክርስቶስ ባሮች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከልብ በመፈጸም ታዘዟቸው...”)።
3. ሠራተኛ ለሥራው ታማኝነት በእግዚአብሔር ይባረካል (“…ምክንያቱም ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው ለሚያደርገው በጎ ነገር ሁሉ ሽልማቱን ከጌታ እንደሚቀበል ታውቃላችሁ...”)።
ቲቶ 2፥9-10 - የሐቀኝነት መርህ
► አንድ ተማሪ ለብድኑ ቲቶ 2፥9-10ን ማንበብ አለበት። የዚህን ምንባብ ትርጉም ተወያዩበት ከዚያም ወደ ምልከታዎ ለመጨመር ከታች ያለውን ዝርዝር ይመልከቱ።
ከቲቶ 2፥9-10 አንዳንድ ማመልከቻዎች፦
1. ሰራተኛው ለቀጣሪው መመሪያ በሚሰጠው ምላሽ አክብሮት ሊኖረው ይገባል (“...የዐጸፋ ቃል እንዳይመልሱላቸው አስተምር...”)። አንድ ሠራተኛ ስለ አሰሪው አክብሮት በጎደለው መንገድ ለሌሎች ሠራተኞች ሲናገር ምን ውጤት ያስገኛል?
2. ሰራተኛው ተጨማሪ ክፍያ ይገባኛል ብሎ ቢያስብም እንኳን (“...አይስረቁ...”) ከአሰሪው አይሰርቅ።
3. ታማኝ ሥራ የወንጌል ምስክር ነው። ታማኝ አለመሆን በወንጌል ላይ ነቀፋ ነው (“...ይኸውም በሁሉም መንገድ የአዳኛችን የእግዚአብሔር ትምህርት ይወደድ ዘንድ...”)።
► አንዳንድ ሰዎች በሥራቸው ሐቀኝነት የሚያጎድልባቸው አንዳንድ ምሳሌዎች ምንድናቸው? አማኝ እንዴት የተለየ መሆን እንዳለበት ግለጽ።
በቲቶ እና በኤፌሶን ውስጥ ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሰው አንድ ሰው ቢቀጥረው እንዴት መሥራት እንዳለበት ይናገራሉ። አንድን ነገር ለመሥራት ወይም አንድን ነገር ለመጠገን ለተቀጠረ ሰው ተመሳሳይ መርሆዎች ይሠራሉ። አንድ ሰው እንዲሠራለት ሚፈልገውን ዓይነት የሥራ ጥራት መሥራት አለበት። የሚሸጥ ነገር የሚያመርት ሰው ገዢዎች የተሻለ ነገር እያገኙ እንደሆነ እንዲያስቡ ጉድለቶችን መደበቅ የለበትም።
ቀጣሪዎች አንድ ሠራተኛ ምን ዓይነት ባሕርያት እንዲኖሩት ይፈልጋሉ? ጥናቶች እንደሚያሳዩት አሠሪዎች ስለ ሥራ አዎንታዊ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ይፈልጋሉ። እምነት የሚጣልባቸው እና ለመማር ዝግጁ የሆኑ ሰዎችን ይፈልጋሉ። ብዙውን ጊዜ ሰዎች የሚቀጠሩት ከሥልጠና ወይም ከችሎታ ይልቅ ስለ ሥራ ባላቸው አመለካከት ነው። እግዚአብሔር አስቀድመን በመፅሐፍ ቅዱስ እንዳየነው ለሥራ ስላለን አመለካከት ያስባል።
ዋጋ ያለው ሰራተኛ የሚያደርጉዎትን ባህሪያት ያዳብሩ። ለማገልገል ዝግጁ መሆን አለብዎት። ታማኝ፣ አስተማማኝ እና ታጋሽ መሆን አለብዎት። አንዳንድ ሥራ አጥ ሰዎች ስለሚያስፈልጋቸው ነገር ብቻ ያስባሉ። ቀጣሪ እርስዎን ለመርዳት አይቀጥርዎትም እንድትረዳው ይቀጥራል። ለአሰሪ ዋጋ የሚሆን ሰው መሆን አለብህ።
አንድ ሰው እንዲህ ሊል ይችላል “ለዚያ ክፍያ ቢከፈለኝ ተግባቢ እና አጋዥ እና ታማኝ እሆናለሁ” ነገር ግን አሠሪዎች ወዳጃዊ ያልሆነን ሰው አይቀጥሩም እና ወዳጃዊ እንዲሆን አይከፍሉትም። ሐቀኛ ያልሆነን ሰው አይቀጥሩም እና ሐቀኛ እንዲሆን አይከፍሉትም። ተግባቢ፣ አጋዥ እና ታማኝ ሰውን ለመቅጠር እየፈለጉ ነው።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ነገሮች የተለያዩ ናቸው። እነርሱን ለመርዳት ፈቃደኛ ከመሆናችን በፊት ሰዎች እንዲሰጡን ወይም ተግባቢ እንዲሆኑ አንጠብቅም። መልካም ነገር ከማድረግህ በፊት እግዚአብሔር ወደ አንተ ይደርሳል እና ይባርክሃል። ነገር ግን ለራስህ ጥቅም ለጸጋ ምላሽ መስጠት መጀመር አለብህ። መስጠት እና ማገልገል ይማሩ እና ፈገግ ይበሉ።
ብቃቶችሆን ያሳድጉ። እነዚያን ችሎታዎች ካላቸው ሰዎች ጋር በመስራት ችሎታን ተማር። ምናልባት ለሌሎች አገልግሎት መስጠት ይችላሉ። ምናልባት እርስዎ የሚሸጡትን ምርት ማምረት ይችላሉ። ምናልባት አንድ ሰብል ማሳደግ ይችላሉ። ከሁሉም በላይ፣ እርስዎን በማይጠቅምበት ጊዜም እንኳ ሌሎችን ለመርዳት አመለካከት ይኑርዎት። እግዚአብሔር አገልግሎትህን ይባርካል።
ማገልገል ማለት ምን ማለት ነው? ማገልገል ማለት የእርስዎን ችሎታ፣ ጊዜ እና ጉልበት ለሌላ ሰው ጥቅም መጠቀም ነው።
ለአሰሪ እየሰሩ ቢሆንም ባይሆንም አገልግሎቱ ከአንዳንድ መብቶችዎን እና ልዩ ጥቅሞችን እንዲለዩ ይጠይቃል። ለምሳሌ ለሌሎች እየሰሩ ከሆነ ጠዋት እንደፈለጋችሁት አርፍዳችው መተኛት አትችሉ ይሆናል እና መስራት የምትፈልገውን በመስራት የስራ ጊዜህን ማሳለፍ አትችልም። የህይወትህን ገፅታዎች ለተቀጠርህበት አላማ አስረክበሃል። የስራ ስምሪት በአለባበስዎ እና ሌሎች ሰዎችን በሚይዙበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።
ለማገልገል የሚሆን ዝግጁነት ብዙ ጥቅሞችን ያስገኛል፦
1. አንዳንድ ፍላጎቶችዎ እንዲሟሉ የሚያደርጉ ግንኙነቶችን ይፈጥራል። ብዙውን ጊዜ ይህ በማይገመት ሁኔታ ይከሰታል ስለዚህ አንድ ነገር ሊያደርጉልዎት ይችላሉ ብለው የሚያስቡትን ሰዎች መርዳት ብቻ አይደለም።
2. በክርስቶስ አካል በሆነው በቤተክርስቲያን ውስጥ ጠቃሚ ቦታ ይሰጥሃል።
3. አንድ ሰው መቅጠር የሚፈልገው ሰው እንድትሆን ያደርጋል።
ሌሎችን ለማገልገል መንገዶችን በመፈለግ አዲስ አስተሳሰብ ለመመስረት ቢጀምሩስ? ኢየሱስም አለ “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ምስጉን ነው” (ሐዋርያት ሥራ 20፥35)። እውነት ያንን ታምናለህ? እርስዎ እንዳመኑት ነው የሚኖሩት?
የሌሎችን ፍላጎት የማሰብ እና በራስዎ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ አለመጠመድ መንፈሳዊ መርሆ አለ (ፊልጵስዩስ 2፥4)። ተግባራዊ መርህም አለ። ያስታውሱ፣ ሰዎችን የሚቀጥሩ ሰዎች ብዙውን ጊዜ የሚቀጥሩትን ሰዎች ለመርዳት አይደለም የሚያደርጉት። አንድን ሰው የሚቀጥሩት ይህ ሰው ያላቸውን ፍላጎት ሊያሟላ ይችላል ብለው ስለሚያስቡ ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ሌላ ሰው እንዲያደርግለት የሚፈልገውን ብቻ ማሰብ ከቻለ መቀጠር አይገባው ይሆናል።
ሰዎች ለመስራት ፈቃደኛ ሲሆኑ ነገሮች ይከሰታሉ። እነዚያ ጥቅማጥቅሞች በድንገት ቢከሰቱ ተአምር የሚመስሉ ነገሮች ናቸው ነገር ግን እግዚአብሔር እነዚህን ጥቅሞች ወደ ህይወቶ የሚያመጣበት የተለመደ መንገድ አለው።
እግዚአብሔር በሚወደው መንገድ እርዳታን ማግኘት እንድትችሉ ለመሥራት ፈቃደኛ ካልሆናችሁ እግዚአብሔር ተአምር እንዲያደርግ ተስፋ ማድረግ፣ መመኘት ወይም መጸለይ ጊዜ ማባከን ነው።
► አንድ ሰው ለአሰሪ ጥሩ ስራን መስራት እንዴት ለወንጌል እድል እንደሚፈጥር ታሪክን ሊያካፍል ይችላል።
► አንድ ሰው በአካባቢያቸው ያለውን ሰው መርዳት የክርስቲያናዊ እንክብካቤን ጥሩ ማሳያ እንደሆነ የሚገልጽ ታሪክ ሊናገር ይችላል።
► ቡድኑ ለስራ ፈት ሰው ስላለው የስራ እድል በጋራ ሃሳቦችን ማንሸራሸር አለበት።
የሰማይ አባት
በፈጠራ ለመስራት ስላለኝ ዕድል አመሰግናለሁ። ሌሎችን ለመርዳት እድሎችን እንድመለከት እርዳኝ። ለራሴ እና ለሌሎች ሀላፊነት ለመውሰድ ስሰራ ፍላጎቶቼን አሟላልኝ።
ቤተሰቤን እንድደግፍ፣ ለቤተክርስትያን እንድሰጥ እና ሌሎችን በችግራቸው መርዳት እንድችል በሀብቶች ባርከኝ።
በሁሉም ኃላፊነቶቼ ውስጥ ታማኝ እና አስተማማኝ እንድሆን እርዳኝ። ፈቃድህ ከሆነ ለታላቅ እድሎች እና ኃላፊነቶች አዘጋጀኝ። ሁል ጊዜ ለእኔ ታማኝ ስለሆንክ አመሰግናለሁ።
አሜን
(1) እነዚህን ምንባቦች አጥኑ፦
ምሳሌ 6፥6-11
ምሳሌ 10፥4-5
ምሳሌ 12፥11, 24, 27
ምሳሌ 13፥4, 11
ምሳሌ 14፥23
ምሳሌ 18፥9
ምሳሌ 20፥13
ምሳሌ 22፥29
ምሳሌ 24፥30-34
ምሳሌ 26፥13-16
ከእነዚህ ምንባቦች ውስጥ ስለ ሥራ እና ስንፍና የነጥቦች እና ማመልከቻዎች ገፅ ይጻፉ።
(2) ከታች ከተዘረዘሩት ርዕሰ ጉዳዮች በአንዱ ላይ አጭር የዝግጅት አቀራረብ (ፕረዘንቴሽን) ለማዘጋጀት ከሌላ የክፍል ጓደኛ ጋር አብረው ይስሩ። (የክፍል መሪው ርዕስ ለእያንዳንዱ ቡድን ይመድባል) በሚቀጥለው የክፍል ጊዜ መጀመሪያ ላይ ፕረዘንቴሽኑን ያካፍሉ።
ሥራ እና የእግዚአብሔር መልክ በሰው ውስጥ
ስራ እና ሃላፊነት ለራስ እና ለሌሎች
አንድ ክርስቲያን ሊሰራበት የሚገባው መንገድ (ይህ ፕረዘንቴሽን በኤፌሶን 6፥5-8 እና በቲቶ 2፥9-10 ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት።)
እግዚአብሔር ብዙውን ጊዜ የሰዎችን ፍላጎት የሚያሟላበት መንገድ
ሥራ እና ከሌሎች ጋር ያለ ግንኙነት
13 lessons · አማርኛ
Your print request has been recorded. Your download should begin shortly.
Download Print-Ready FileFree to print for ministry use. No changes to content, no profit sales.
SGC exists to equip rising Christian leaders around the world by providing free, high-quality theological resources. We gladly grant permission for you to print and distribute our courses under these simple guidelines:
All materials remain the copyrighted property of Shepherds Global Classroom.
Questions? info@shepherdsglobal.org
Total
$21.99Added to Cart!
By submitting your contact info, you agree to receive occasional email updates about this ministry.
Download audio files for offline listening
No audio files are available for this course yet.
Check back soon or visit our audio courses page.
Share this free course with others