የትምህርት ዓላማዎች
በዚህ ትምህርት መጨረሻ ተማሪው የሚከተሉትን ማድረግ ይኖርበታል፦
(1) እያንዳንዱ ሰው ዋጋ ያለው እና በእግዚአብሔር አምሳል በመፈጠሩ ሊከበር የሚገባው መሆኑን ማመን።
(2) በእርሱ አካባቢ ለተበደሉ ሰዎች የፍትህ እና የምሕረት ሥራዎችን ለመፈጸም ኃላፊነትን መውሰድ።
(3) ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ሰዎችን ሁሉ በክብር ለመያዝ ቃል መግባት።
Lesson
Playlist
Search through all lessons and sections in this course
Searching...
No results found
No matches for ""
Try different keywords or check your spelling
1 min read
by Stephen Gibson
በዚህ ትምህርት መጨረሻ ተማሪው የሚከተሉትን ማድረግ ይኖርበታል፦
(1) እያንዳንዱ ሰው ዋጋ ያለው እና በእግዚአብሔር አምሳል በመፈጠሩ ሊከበር የሚገባው መሆኑን ማመን።
(2) በእርሱ አካባቢ ለተበደሉ ሰዎች የፍትህ እና የምሕረት ሥራዎችን ለመፈጸም ኃላፊነትን መውሰድ።
(3) ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ሰዎችን ሁሉ በክብር ለመያዝ ቃል መግባት።
Dale Carnegie How to Win Friends and Influence People በተሰኘው መጽሃፉ ታዋቂ ነበር። ሰዎች ሁሉ እንደ ሰው በተፈጥሯቸው ጠቃሚ ስለሆኑ ትኩረት እና ክብር እንደሚገባቸው ያምን ነበር። Dale Carnegie Institute የተቋቋመው መርሆቹን ለማስተማር ነው።
አንዴ Dale Carnegie Institute እንዴት ወዳጃዊ መሆን እና ከሰዎች ጋር ግንኙነት መፍጠር እንደሚችሉ ለንግድ ባለሙያዎች በሚያስተምር የምሽት ክፍል ላይ ነበር። ተማሪዎቹ ፈተናውን ሲወስዱ በአንድ ጥያቄ ተገረሙ። ያልተጠበቀው ጥያቄ “ከክፍል ስትወጡ ሁልጊዜ ሎቢውን የምታጸዳውን ሴት ማን ትባላለች?” የሚል ነበር። ተማሪዎቹ ከክፍል ወጥተው ወደ ቤት ሲሄዱ ብዙ ጊዜ በዚያ አልፈዋል ነገር ግን እንዴት ወዳጃዊ መሆን እና ግንኙነት መፍጠር እንደሚችሉ ከተማሩበት ክፍል እየመጡ ቢሆንም ለትኩረት ያህል አስፈላጊ አድርገው አላዩዋትም። አዲሶቹን ክህሎቶቻቸውን ከጠቃሚ ሰዎች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ብቻ መጠቀም እንዳለባቸው ገምተው ነበር።
በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ሰዎች ሁሉ የአንድ አካል ማለትም የክርስቶስ አካል ናቸው “በአይሁድና በግሪክ፣ በባሪያና በነጻ ሰው፣ በወንድና በሴት መካከል ልዩነት የለም፤ ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ናችሁ” (ገላትያ 3፥28)።
የሉቃስ ወንጌል ከኢየሱስ ጋር ስለተነጋገረ አንድ ሕግ ዐዋቂ ይነግረናል። ሰውየው ሕጉ ባልንጀራውን እንደ ራሱ እንዲወድ እንደሚያዝ ያውቅ ነበር፤ ነገር ግን መውደድ ያለበት የተለየ ቡድን ያላቸውን ሰዎች ብቻ እንደሆነ አስቦ ነበር። ኢየሱስን “ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው?” ሲል ጠየቀው (ሉቃስ 10፥29)። ይህ ጥያቄ ሁሉንም ሰው መውደድ እንደሌለበት ያለውን ግምት ያሳያል።
የሁሉም ባሕል ሰዎች ተመሳሳይ ሥነ ምግባር አላቸው። ስርቆት፣ ግድያ እና ጭቆና ስህተት መሆናቸውን ያውቃሉ። ሆኖም ግን ሁሉም ሰው ፍትሃዊ አያያዝ ይገባዋል ብለው አይሰማቸውም። ምናልባት ከጓደኛቸው አይሰርቁም ነገር ግን ከማያውቁት ሰው ይሰርቁ ይሆናል። ምናልባት የገዛ ሀገራቸውን ሰው አይገድሉም ነገር ግን የባዕድ አገር ሰው ይገድሉ ይሆናል። ምናልባት ዘመዶቻቸውን አይጨቁኑም ነገር ግን የሚጠሉትን ብሔር ይጨቁኑ ይሆናል።
የክርስቶስ ተከታዮች እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር አምሳል ወሰን በሌለው ዋጋ እንደተፈጠረ ያምናሉ።
አንድ መልአክ ለሰዎች በሚገለጥበት ጊዜ ሁሉ በመፅሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸው፣ የእርሱ የመጀመሪያ ቃላቶች “አትፍሩ” የሚሉ ነበሩ፣ ምክንያቱም መገኘቱ እጅግ አስደናቂ እና ድንቅ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በመላእክት ፊት በመውደቅ ለመምለክ ፍላጎት ነበራቸው።[1] ነገር ግን ሰዎች ከመላእክት የበለጠ አስፈላጊ ናቸው (1ኛ ቆሮንቶስ 6፥3)።
ዝቅተኛ ደረጃ ያለው፣ ያልተማረ፣ የማሰብ ችሎታ የሌለው፣ መጥፎ ጠባይ ያለው፣ ችሎታ የሌለው፣ ምንም ተጽእኖ የሌለበት፣ አስጸያፊ ገጽታ ያለው እና የሚያፈገፍግ ስብዕና ያለው ለማኝ የሆነ ሰው ሊያጋጥሞት ይችላል፣ ነገር ግን እርሱ ዘላለማዊ ውጤት ያላቸውን ውሳኔዎችን እያደረገ ነው። እርሱ በእግዚአብሔር ከተዋጀ በምድር ላይ ካየነው ሁሉ የላቀ ፍጡር ይሆናል።[2] ስለዚህም ክብር ይገባዋል።
► አንድ ተማሪ ለብድኑ ገላትያ 3፥28ን ያንብብ።
ይህ ጥቅስ ሰዎች ብዙውን ጊዜ የሚመደቡባቸውን ሦስት መንገዶች ይጠቅሳል ጎሣ፣ ማህበራዊ መደብ እና ጾታ ናቸው። ማህበራዊ መደብ ኢኮኖሚያዊ ደረጃን ያጠቃልላል። እንደ ዕድሜ፣ የትምህርት ደረጃ እና ችሎታ ያሉ ሌሎች ምደባዎችን ማከል እንችላለን። ከእነዚህ ምድቦች ውስጥ አንዳቸውም የእግዚአብሔርን ለሰው ያለውን ዋጋ የሚነኩ አይደሉም።
► አንድ ሰው ከሌሎች ሰዎች የበለጠ ዋጋ ያለው ሊሆን ይችላልን? ግለጽ።
ከፍተኛ የማሰብ ችሎታ፣ የትምህርት ደረጃ፣ ክህሎት፣ አካላዊ ጥንካሬ፣ የአመራር ልምድ ወይም ገንዘብ ያለው ሰው አንዳንድ ነገሮችን ለማከናወን የበለጠ ጠቃሚ ነው። ሆኖም በእነዚያ ባህሪያት የተነሳ አንድን ሰው እንደ ሰው የበለጠ ዋጋ ያለው አድርጎ መቁጠር ስህተት ነው። እነዚያ ባህርያት ተግባራዊ ዋጋ አላቸው ነገር ግን በእግዚአብሔር አምሳል የተሰራው የሰው ልጅ ማለቂያ የሌለው አስፈላጊ ተፈጥሮአዊ እና ዘላለማዊ ዋጋ አለው።
ሰዎች የአንድ ብሔረሰብ ሰዎች ሁሉም የተወሰኑ ባህሪያት አላቸው ብለው ያስባሉ። አንዳንድ ጊዜ እነዚህ መግለጫዎች የቆዳ ቀለምን በመጥቀስ “ነጭ ሰዎች ሁል ጊዜ ________” ወይም “ጥቁር ሰዎች ሁሉም ____ ናቸው ይላሉ።”
አንዳንድ ጊዜ መግለጫው እንደ ሄይቲ ወይም ጀርመኖች ወይም ጃፓን ያሉ ዜግነቶችን ይመለከታል። አንዳንድ ጊዜ የበለጠ የተወሰነ ይሆንና በሀገር ውስጥ ያለን ጎሳ ወይም ብሔረሰብ ስም ይጠቅሳል።
ሰዎች ስለ ሰዎች ምድቦች የሚናገሩት መግለጫ አንዳንድ ጊዜ አበረታች ናቸው ነገር ግን ብዙ ጊዜ አአሳሳቢ ናቸው። መግለጫው የዚያ ቡድን እያንዳንዱ ሰው የተወሰነ ስህተት አለበት ሊል ይችላል።
ሰዎች ስለ ብሔረሰቦች ወይም ዜጎች የሚሰጡት አሳሳቢ መግለጫ ምሳሌዎች እኚህ ናቸው። የተለያዩ ብሔረሰቦች ስሞች በባዶ ቦታ ውስጥ ይገባሉ።
____ ሰነፍ ናቸው።
____ በተደጋጋሚ ይሰክራሉ።
____ እድሉን ካገኙ ይሰርቃሉ።
____ በተደጋጋሚ ይጣላሉ።
____ ስራውን በጥሩ ሁኔታ አይጨርሱም።
____ በትምህርት ቤት ጥሩ ለመስራት በቂ ብልሀት የላቸውም።
____ በፍጥነት ይናደዳሉ።
____ ሁል ጊዜ ይዋሻሉ።
የጎሳ ልዩነቶች እንዳሉ ግልጽ ነው እና እነዚህ ልዩነቶች ከአካላዊ ገጽታ በላይ ናቸው። አንድ ብሔረሰብ በአካልና በአእምሮ ችሎታቸው ምክንያት በአንዳንድ ስፖርቶች ወይም የሥራ ዓይነቶች የላቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
የሰዎች ብድን ባህላዊ ባህሪያት አሉት። ባህል ሰዎች ለአንዳንድ ሁኔታዎች በተወሰኑ መንገዶች ምላሽ እንዲሰጡ ያስተምራል፣ ስለዚህ አንዳንድ ድርጊቶችን ከተወሰኑ የባህል ሰዎች መጠበቅን እንማራለን።
የአንድ ቡድን አካላዊ እና ባህላዊ ባህሪያትን ማስተዋል ስህተት አይደለም። ነገር ግን በብሄሩ ወይም በባህሉ ምክንያት የአንድን ሰው ባህሪ መገምገም ስህተት ነው። ከየትኛውም ጎሳ የመጣ ሰው አምላካዊ፣ ታማኝ እና ደግ ሊሆን ይችላል። እንደ ግለሰብ ሳታውቁት እርሱ መጥፎ ጠባይ እንዳለው ማየቱ ስህተት ነው።
የግላዊ ልምዶቻችን ሌሎች ሰዎችን በምንመለከትበት መንገድ ላይ ተጽእኖን ያሳድራሉ። አንድ ሰው በሌላ ብሔር ተወላጆች በደል ቢደርስበት የዚያ ብሔረሰብ አባላት በሙሉ አንድ እንደሆኑ ሊሰማው ይችላል። ግለሰቡ የዚያ ጎሳ አባል የሆነ ሰው በተደጋጋሚ ቢበድለው ወይም ይህ መጥፎ ገጠመኙ በልጅነቱ ከተከሰተ ይህ ስሜት በበለጠ ይጠናከራል።
በሁለት ብሄረሰቦች መካከል የረዥም ጊዜ ግጭቶች እርስበርስ ጥላቻ ያላቸው ትውልዶችን ሊፈጥር ይችላል።
አንድ ልጅ ወላጆቹና ሌሎች ጎልማሶች ስለ አንድ ጎሣ ሰዎች ሲናገሩ ሲሰማ ስለዚያ ጎሣ ያለው አመለካከት ይመሰረታል።
አንድ አማኝ ለብሔር ብሔረሰቦች ያለውን አመለካከት በመመርመር ፍትሕና ፍቅርን እንዲያሳይ እግዚአብሔር እንዲረዳው መጸለይ አለበት። እግዚአብሔር ለእኛ እንደሚያስብ እንዲሁ ደግሞ ለሌሎች እንደሚያስብና ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ ብንይዛቸው እንደማይደሰት ማስታወስ አለብን።
በብሉይ ኪዳን የሚገኘው የዮናስ ታሪክ አስተማሪ ነው። ዮናስ ከእግዚአብሔር የሸሸበትን ምክንያት ይነግረናል፦
ወደ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁትስ ይህን አልነበረምን? ፈጥኜ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል የተነሣሁትም ለዚሁ ነበር፤ አንተ ቸርና ርኅሩኅ፣ ለቍጣ የዘገየህ አምላክ፣ ምሕረትህ የበዛ፣ ጥፋትንም ከማምጣት የምትመለስ እንደ ሆንህ ዐውቃለሁ። አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ውሰድ፤ ከመኖር መሞት ይሻለኛልና” (ዮናስ 4፥2-3)።
ዮናስ ከእግዚአብሔር ፊት ሸሽቷል ምክንያቱም ለአሦራውያን ካለው ጥልቅ ጥላቻ የተነሳ እና እግዚአብሔር በነነዌ ሰዎች መካከል እንዲሠራ የጠየቀው ጥሪ እግዚአብሔር ለእነርሱ መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ትልቅ ዕድል እንዳለው ስለሚያውቅ ነው።
የዘር ማህበራዊ ጽንሰ ሀሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽንሰ ሀሳብ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ሁሉ አንድ ዘር እንደሆኑ ያስተምራል ይህም የሰው ዘር ነው፦ “የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ወገን ፈጥሮ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ አደረገ፤ የዘመናቸውን ልክና የመኖሪያ ስፍራቸውንም ዳርቻ ወሰነላቸው” (ሐዋርያት ሥራ 17፥26)።
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን በምድር ላይ ላሉ ብሔረሰቦች ሁሉ ወንጌልን እንድትደርስ ጠርቷታል (ሐዋርያት ሥራ 1፥8)። የየትኛውም ብሄረሰብ ቢሆን የሰው ነፍስ ዋጋ አንድ ነው።
ሰዎች ምድራዊ፣ ዓለማዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች የመቀበል ዝንባሌ ስላላቸው የሰዎችን ዋጋ ለማስቀመጥ የተሳሳተ መንገድ ይጠቀማሉ። ብዙ ማህበረሰቦች አንዳንድ ሰዎችን ዝቅ አድርገው ይመድቧቸዋል እና ከሰው ያነሱ እንደሆኑ አድርገው ይመለከቷቸዋል።
ከዚህ በታች የተለያዩ ማህበረሰቦች የተወሰኑ የሰዎች ምድቦችን ባለማክበር የያዙባቸው መንገዶች ምሳሌዎች ዝርዝር አለ። ከእነዚህ ልማዶች መካከል አንዳንዶቹ ታሪካዊ ናቸው ሌሎቹ ደግሞ አሁንም በመተግበር ላይ ናቸው።
የሰዎች ምድቦችን ያለማክበር እውነተኛ ምሳሌዎች፦
አረጋውያን ከአሁን በኋላ ጠቃሚ አይደሉም ስለዚህ እንዲሞቱ በገለልተኛ ቦታ ይቀራሉ።
ሰዎች ከሌላ ብሔር የመጡ ሰዎችን በባርነት ይይዛሉ እና ሊሸጡዋቸው ወይም እንደፈለጉ ሊያደርጉዋቸው ይችላሉ።
ንግዶች የአንድ ብሄር ተወላጆችን እንደማይቀጥሩ የሚገልጽ ምልክት ይለጥፋሉ።
ሴቶች እንደ ባሎቻቸው ንብረት ይቆጠራሉ፣ ባሎቻቸው እደፈለጉ ያደርጓቸዋል።
ቤተሰቦች ወንድ ልጆችን ስለፈለጉ ጨቅላ ሴቶች እንዲሞቱ ይደረጋሉ።
የአንድ ሀገር መንግሥት የአንድ ብሔር ሁሉንም ተወላጆች ለመግደል ወታደሮችን ወደ አንድ ክልል ይልካል።
ልጆች የአእምሮ ወይም የአካል እክል ስላለባቸው ይተዋሉ።
አንድ ሀገር ሴት መኪና እንዳትነዳ ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንዳትማር የሚከለክል ህግ አለው።
የጋራ ብሄራዊ ቋንቋ የሚናገሩ ግን በትምህርት ቤት የሚማሩትን ቋንቋ የማይናገሩ ሰዎች በመንግስት ቢሮ ውስጥ ለራሳቸው እንዲናገሩ አይፈቀድላቸውም።
ሰዎች የተቀጠሩት ከአፍሪካ ስሞች ይልቅ የእንግሊዝኛ ስም ስላላቸው ነው።
ሴት ልጆች በአባቶቻቸው ለባርነት ወይም ለሴተኛ አዳሪነት ሊሸጡ ይችላሉ።
እናቶች ልጅ ለመውለድ ዝግጁ ስላልሆኑ ሕፃናት ከመወለዳቸው በፊት ይገደላሉ።
አንዳንድ ፍልስፍናዎች እና ሃይማኖቶች የሰዎች ምድቦችን በደል ይደግፋሉ።
እግዚአብሔር የለም የሚሉ የዝግመተ ለውጥ አራማጆች ሰዎች በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩ ናቸው ብለው አያምኑም። ዘመናዊ ሰዎች የተገነቡት ደካማ እና የማሰብ ችሎታ የሌላቸውን የሰው ልጅ ልዩነቶችን በመወዳደር እና በማጥፋት ነው ብለው ያምናሉ። “የተሻለ ብቃት ያለው ይተርፋል” የሚለው እንደፈጠረን ያምናሉ። ይህም እውነት ከሆነ ሰዎች ደካማ የሆኑትን የሰው ልጅ ዓይነቶች ማጥፋታቸውን መቀጠላቸው ተገቢ ይሆናል። ነገር ግን ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር አምሳል እንደተፈጠሩ እና በዚህም ለእግዚአብሔር ልዩ እንደሆኑ እናውቃለን።
ብዙ የአለም ሀገራት ዶክተሮች ህጻናት ከመወለዳቸው በፊት እንዲገድሉ ይፈቅዳሉ። አንዳንድ መንግስታት ከመጠን ያለፈ የህዝብ ቁጥር የተነሳ ህፃናት እንዲገደሉ ጠይቀዋል። በብዙ አገሮች እናቶች ልጅ ለመውለድ ጥሩ ሁኔታ ላይ ስላልሆኑ ህፃናት ከመወለዳቸው በፊት እንዲገደሉ ዶክተሮችን ይጠይቃሉ። ያልተወለዱ ሕፃናት ሲገደሉ በእግዚአብሔር አምሳል እንዳልተፈጠሩና ዋጋ እንደሌላቸው ይቆጠራል። መብታቸው እየተጣሰ ነው እናም ለራሳቸው መናገርም ሆነ መከላከል አይችሉም።
እንደ ሂንዱይዝም እና ቡድሂዝም ያሉ ሃይማኖቶች ሰዎች ከዚህ በፊት በነበሩት የህይወት ዘመናቸው በፈጸሙት የተሳሳተ ድርጊት ምክንያት ይሰቃያሉ ብለው ያምናሉ። የተጨቆኑ ሰዎች ያላቸው ደረጃ ይገባቸዋል ብለው ያምናሉ። አንድ ሰው መከራን እና ጭቆናን በጥሩ ሁኔታ ከተቀበለ በሚቀጥለው ጊዜ የተሻለ ሕይወት ሊኖረው እንደሚችል ያምናሉ። እነዚያ ሃይማኖቶች የተጨቆነውን ሰው ለመርዳት ትንሽ ምክንያት ይሰጣሉ ምክንያቱም ሰውዬው በአስፈላጊ ሂደት ውስጥ እያለፈ ነው ብለው ስለሚያስቡ ነው።
የተሳሳቱ ፍልስፍናዎች እና ሃይማኖቶች ሰዎች በሰዎች ላይ የሚደርሰውን አሰቃቂ እንግልት እንዲታገሡ ያደርጋቸዋል። ማህበረሰቦች የከፍተኛ ማህበራዊ ኢፍትሃዊነት ሁኔታዎችን እንደ መደበኛ ይቀበላሉ። አማኞች የተለያዩ ናቸው። በእግዚአብሔር አምሳል የልዩ ፍጥረት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ለሰው ልጅ ዋጋ ብቸኛ በቂ መሠረትን ይሰጣል።
► በማህበረሰብዎ ውስጥ ምን ዓይነት የሰዎች ምድብን አለማክበር ድርጊት የተለመደ ነው?
እንደ ብዙዎቹ የኢየሱስ ምሳሌዎች የደጉ ሳምራዊ (ሉቃስ 10፥29-37) ታሪክ ለአድማጮቹ አስደንጋጭ ነበር። ካህኑና ሌዋዊው የተጎዳውን ሰው ሳይረዱት እንዴት እንዳለፉ ሲናገር ማንም አልገረመውም። ካህናቱ እና ሌዋውያኑ የሃይማኖታዊ ተቋማት አካል ነበሩ ነገር ግን ሰዎች በገንዘብ እና በስልጣን የተበላሹ እንደሆኑ መስሏቸው ነበር።
አድማጮቹ ሦስተኛው ሰው የታሪኩ ጀግና ይሆናል ብለው ጠብቀው ነበር ነገር ግን ሳምራዊ በመሆኑ ደነገጡ እና አዝነው ነበር። ሳምራውያን በዘር የተደባለቁ እና በሃይማኖታቸው ግራ የተጋብ ነበሩ። አይሁድ በሁለቱም ምክኒያቶች ይንቋቸው ነበር።
አንድ የአይሁድ ሰው ኢየሱስን “ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው?” የሚለውን ጥያቄ እንደጠየቀው አስታውሱ። ኢየሱስ እርሱ የሚወዳቸውን ሰዎች እንዲገልጽ ፈልጎ ነበር፣ አዲስ ጠባብ ምድብ ያስቀምጣል። እንደ አብዛኞቹ የዓለም ሰዎች የሞራል ግዴታዎቹ ለተመረጡት ሰዎች ብቻ እንደሆኑ እና ለሌሎች ግድ እንደሌለበት አስቦ ነበር።
ኢየሱስ ለሚያጋጥመን ሰው ሁሉ እንክብካቤ ልናሳይ እንደሚገባ በማሳየት ለጥያቄው መልስ ሰጥቷል። የምናገኘው ማንኛውም ሰው ጎረቤታችን ነው። ኢየሱስ ግን “መልካም ባልንጀራ ማን ነው?” “ወይም ይህን ፍቅር የሚያሳየው ምን ዓይነት ሰው ነው?” የሚል ማንም ያላቀረበለትን ጥያቄም መለሰ። በማህበረሰቡ ዘንድ የማይከበር ሰው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እና እግዚአብሔር ማየት የሚፈልገውን ፍቅር የሚያሳይ ሰው ሊሆን እንደሚችል አሳይቷል።
ሐዋርያው ያዕቆብ ቤተክርስቲያን ሰዎችን በአለም መስፈርት እንዳታከብር ያስጠነቅቃል።
► አንድ ተማሪ ለብድኑ ያዕቆብ 2፥1-9ን ያንብብ። ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነን ምን ነገር አብያተ ክርስቲያናት ሲያደርጉ አይተሃል?
በምድር ላይ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ብዙ ሰዎች በእግዚአብሔር የተከበሩ ሰዎች አይደሉም። እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙ ብዙ ሰዎች በምድር ላይ አልተከበሩም። ኢየሱስ በዘላለም ውስጥ የብዙ ሰዎች አቋም እንደሚለወጥ ተናግሯል (ማቴዎስ 19፥30)።
ክርስቲያን ወንድሞች በሚሰበሰቡበት ጊዜ ድሃው ሰው እንደ ክርስቲያን ወንድም ስለሚከበር በዓለም ላይ ያላገኘውን ክብር ያገኛል። ባለጠጋ በዓለም ሳለ ያለውን ደረጃ በቤተክርስቲያን ያጣዋል ምክንያቱም ገንዘቡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሌሎች በላይ ስለማያደርገው ነው (ያዕቆብ 1፥9-10)።
ባሪያ ማለት የሌላ ሰው ንብረት ሆኖ የተያዘ ሰው ነው። ባርነትን በሚፈቅዱ አብዛኞቹ ሀገራት ባሪያው እንደ ሰው ምንም አይነት መብት የለውም። ባለቤቱ ባሪያውን እንስሳ ወይም ማሽን ይመስል የፈለገውን እንዲያደርግበት ይችላል። የባሪያው የራሱ ፍላጎቶች እና ምኞቶች ለባለቤቱ ፈቃድ ይገዛሉ። ባልና ሚስት በባለቤታቸው ሊለያዩ ይችላሉ፣ ልጆችም ከወላጆቻቸው ሊወሰዱ ይችላሉ።
በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ባርነትን ገድቧል እናም ለባሪያው የተወሰኑ መብቶችን ጠብቋል (ዘፀአት 21፥1-11፣ 26-27)። በእነዚያ ጊዜያት ለባሪያ መብቶች መጨነቅ በጣም ያልተለመደ ነበር። በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር እርሱ የሰዎች ሁሉ ጌታ እንደሆነና ማንንም ስለ ማዕረግቸው ሲል እንደማይደግፍ ተናግሯል እናም የባሪያዎች ጌታ ቸር እና ፍትሃዊ መሆን አለበት (ኤፌሶን 6፥9)። አንድ ባሪያ ለእያንዳንዱ ሰው እንደሚሰጥ ክብር ለእርሱም የሚገባው እንዲደረግ ይህን ግምት ውስጥ ማስገባት ይገባል የሚለው መሠረታዊ ሥርዓት በመጨረሻ መጽሐፍ ቅዱስ ከፍተኛ ተጽዕኖ በሚያሳድርባቸው ሀገራት ውስጥ ባርነት እንዲወገድ አድርጓል።
ባርነት አሁንም በተለያዩ ቦታዎች በብዙ አይነቶች አለ። ለምሳሌ በአንዳንድ ቦታዎች ልጆች ለስራ ወይም ለወሲብ በወላጆች ይሸጣሉ። አንዳንድ ጊዜ ልጆች ከበሽታ ወይም ከእርግማን ለመዳን በክፍያ ለባዕዳዊ ቤተመቅደሶች ይሰጣሉ። አንዳንድ ጊዜ ሴቶች ያለፍላጎታቸው በሴተኛ አዳሪነት ይጠበቃሉ። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ለባርነት ዓላማ ወደ ሌላ ሀገር በድብቅ ይወሰዳሉ።
የኢኮኖሚ ነፃነት በሌለበት ቦታ ሁኔታዎች በከፊል ባርነትን ሊመስሉ ይችላሉ። ሰዎች የራሳቸውን ንግድ የመምራት ነፃነት የላቸውም። አንድ ሰው ሥራውን ለተሻለ ነገር ለመለወጥ እድሉ ትንሽ ነው። አንዳንድ ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን ትንሽ ለሚመግብ ደመወዝ ይሠራሉ። ከመሠረታዊ ምግብ በስተቀር ምንም ነገር አይገዙም። የሕክምና እንክብካቤ ማግኘት አይችሉም። ምንም ያህል ቢደክሙ በተሻለ ቤት ውስጥ መኖር አይችሉም ምክንያቱም ገንዘቡ ለፍላጎታቸው በቂ አይደለም። ቀጣሪዎቻቸው ተጨማሪ ክፍያ አይከፍሉም ምክንያቱም ሁልጊዜ በዝቅተኛ ክፍያ የሚሰሩ ሰዎችን ማግኘት ስለሚፈልጉ ነው።
የኢኮኖሚ ጭቆና ውስብስብ እና የአሰሪዎች ስህተት ብቻ አይደለም። በአንዳንድ አገሮች ብዙ የሚገኙ ሠራተኞች ግን ጥቂት ፋብሪካዎች እና ትላልቅ ንግዶች አሉ። አንድ መንግሥት በሙስና ከተዘፈቀ ከፍተኛ ግብርና ጉቦ በመጠየቅ ትልልቅ የንግድ ሥራዎችን እንዳይጀምር ሊያደርግ ይችላል። ብዙ ቢዝነሶች ቢፈቀዱ የሰራተኞች ደሞዝ ከፍ ያለ ይሆን ነበር ምክንያቱም ሰራተኞቹ የት እንደሚሰሩ መምረጥ ስለሚችሉ እና ንግዶች በተሻለ ደሞዝ እና ሁኔታዎች ሊስቧቸው ይገባል። ጥቂት ቢዝነሶች ስለተፈቀደላቸው እና ሰራተኞችም ለመቀጠር ጥቂት አማራጮች ስላሏቸው አሰሪዎች ለሰራተኞቻቸው ዝቅተኛ ደሞዝ ይከፍላሉ። ሠራተኞች የገንዘብ ፍላጎታቸውን ለማሟላት በቂ ገቢ ማግኘት አይችሉም።
የመንግስት አላማ ህዝብን ከጥቃትና ነፃነቱን በመጠበቅ ማገልገል ነው። መሰረታዊ የሰው ልጅ ነፃነቶች ሃሳብን የመናገር፣ ሀይማኖት የመከተል፣ ለጥቅም የመስራት እና ንብረት የማፍራት መብት ናቸው። አንድ ሰው እነዚህን ነገሮች እንዲያደርግ የማይፈቀድለት ከሆነ እንደ ሙሉ ሰው አይቆጠርም።
አንዳንድ ጊዜ በአንድ ቦታ ያሉ አማኞች ሁኔታዎችን እንደ መደበኛ ይቀበላሉ እና በኢኮኖሚ የተጨቆኑ ሰዎችን ለመርዳት አይሞክሩም።
ሀና ምንም ሥራ በማይገኝበት ትንሽ መንደር ውስጥ ትሰራ ነበር። እሷም ሶስት ልጆቿን ከአያታቸው ጋር ትታ ወደ ከተማዋ ሄደች በፓስተር ቤት አገልጋይ ሆና በመስራትም በየወሩ ትንሽ ገቢ ታገኝ ነበር። ልጆቿን እምብዛም አታያቸውም። ብዙ ሰዎች እናት እንደዚህ ከልጆቿ መለየቷ ጥሩ እንደሆነ አድርገው አይመለከቱትም ነገር ግን አማኞች እንኳን በሃና አይነት ሁኔታ ውስጥ ያሉትን ይቀጥራሉ። አንድ ሰው በትንሽ መጠን ለመሥራት ፈቃደኛ በሚሆንበት ጊዜ ለምን የበለጠ መክፈል እንዳለባቸው ያስባሉ? ከልጆቿ ተለይታ ለመሥራት ምርጫ ካደረገች ለምን እነርሱ ስለዚህ ያስባሉ።
► አማኞች በሀና ሁኔታ ውስጥ ጣልቃ የመግባት ግዴታ አለባቸውን? እንዴት?
የአሞጽ መጽሐፍ ስለ ኢኮኖሚያዊ ጭቆና ብዙ ጊዜ ይናገራል። በአሞጽ 5፥11-12 ነቢዩ ስለ ጉቦ ሲናገር ዳኞች በገንዘብ ከሰው ወገን እንዲቆሙና ፍትሕ ለድሆች እንደማይደርስ ተናግሯል። በአሞጽ 8፥4-6 ነቢዩ ድሆችን ለማጭበርበር የሐሰት መለኪያ የሚጠቀሙ ሰዎችን ያወግዛል። በአሞጽ 4፥1 ላይ ሴቶች ደግሞ ባሎቻቸው ድሆችን በመጨቆን ያገኙትን የቅንጦት ኑሮ ቢኖሩ ጥፋተኞች ናቸው ብሏል። ነቢዩ ፍትሕ እንደ ወንዝ መፍሰስ አለበት (አሞጽ 5፥24) በማለት ተናግሯል፤ ይህም ማለት የበዛና ለሁሉም የሚገኝ መሆን አለበት።
እያንዳንዱ ሰው ወሰን የለሽ ዋጋ ያለው መሆኑ በሰዎች መካከል የሥልጣን መዋቅር መኖር የለበትም ማለት አይደለም። እኩል ዋጋ ማለት እኩል ስልጣን ማለት አይደለም። ለምሳሌ የሥላሴ አካል ሁሉ ፍጹም እና እኩል አምላክ ቢሆንም ወልድ ግን ለአብ ተገዝቷል (ዮሐንስ 6፥38)። እግዚአብሔር ሚስት ባሏን እንድትታዘዝ አዟል ይህ ማለት ከእርሱ ታናሽ ናት ማለት አይደለም (ኤፌሶን 5፥22)። እግዚአብሔር ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲታዘዙ ነግሯቸዋል ይህ ማለት ግን ከዕድገት በስተቀር ከወላጆቻቸው ያነሱ ናቸው ማለት አይደለም (ኤፌሶን 6፥1)።
እግዚአብሔር መንግሥትን አቋቋመ (ሮሜ 13፥1-5)። በቤተክርስቲያንም ሥልጣንን አቋቁሟል (ዕብራውያን 13፥17)።
ሁሉም መሪዎች አገልጋዮች መሆናቸውን ማስታወስ አለባቸው (ማቴዎስ 20፥25-28)። በመምራት ማገልገል ማለት ለተከተሉት ጥቅም መምራት ማለት ነው። መሪው ለራሱ ጥቅም አይመራም ነገር ግን እርሱን የሚከተሉትን ለማገልገል የራሱን ጥቅም መስዋዕት ያደርጋል።
► አንዳንድ ሰዎች ከሌሎቹ የበለጠ አስፈላጊ ሲሆኑ በሌላ መልኩ ደግሞ ሁሉም ሰዎች እኩል ጠቀሜታ እንዳላቸው እንዴት ይገልፁታል?
ሁሉም ሰዎች በቤተክርስቲያኑ ቤተሰብ እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው ያረጋግጡ።
አረጋውያን እንደሚያስፈልጋቸው ይታወሱ እና ይረዳሉን?
ለልጆች ቦታ ይሰጣቸዋልን እና ለደረጃቸው የሚመጥን ትምህርት እና ማበረታቻ ይሰጣቸዋልን?
ድሆች በቤተክርስትያንዎ ውስጥ አቀባበል እና ምቾት ያገኛሉን?
በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎችን በሀብታቸው ወይም በማህበረሰቡ ውስጥ ስላላቸው ክብር ከማክበር ይቆጠባሉን?
ከሁሉም ብሔረሰቦች የሚመጡ ሰዎች ኅብረት ለማድረግ፣ በቤተክርስቲያን ሕይወት እና አገልግሎት ውስጥ ለመካፈል አቀባበል ይደረጋልን?
በእናንተ አካባቢ ወንጌል ሊሰበክለት የሚያስፈልግ ብሔር አለን?
በአካባቢያችሁ የተጨቆኑ ሰዎች አሉን የሚከራከርላቸው ሰውን የሚፈልጉ አሉን?
ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ቤተሰብ የሁሉንም ሰዎች ዋጋ ማሳየት ይኖርበታል። ባልና ሚስት ሁለቱም መከበር አለባቸው። ፍላጎታቸው ሊታሰብበት ይገባል። ህጻናት ችላ ሊባሉ ወይም እንደ አላስፈላጊ ሊቆጠሩ አይገባም። ልጆች በአግባቡ መገሠጽ አለባቸው። ባልንጀራህን እንደዚያ ለማድረግ ካለህ መብት በላይ ከልጅህ ወይም ከሚስትህ ጋር ጠበኛ የመሆን መብት የለህም።
ድሆችን ክብራቸውን በሚያጠናክር መልኩ ልንረዳቸው ይገባል። ድሆችን እያዋረዳችሁ ራሳችሁን ለማክበር በአደባባይ አትስጡ። ለድሀ ሰው የሚፈልገውን እንዲያገኝ ፍትሃዊ መንገድ ብታቀርቡለት ምርጫ ማድረግ ስለሚችል ክብሩ የተጠበቀ ነው እና ትርፍ ለማግኘት ይሰራል። ከሁሉ የተሻለው እርዳታ ድሆችን ሁኔታቸውን ለመለወጥ እድል ይሰጣቸዋል።
የብሉይ ኪዳን ነቢያት እግዚአብሔር ሕዝቡ የተጨቆኑትን ነጻ እንዲያወጡ እንደሚፈልግ አጽንኦት ሰጥተው ነበር (ኢሳያስ 58፥6)።
አዲስ ኪዳን ኢየሱስ በድሆች መካከል መጣ የሚለው እውነታ ላይ አጽንዖት ይሰጣል (2ኛ ቆሮንቶስ 8፥9)። እርሱ የተወለደው እንስሳት በሚጠበቁበት ስፍራ ነው (ሉቃስ 2፥7)። አብዛኞቹ ጓደኞቹ እና ተከታዮቹ የሚሰሩ ሰዎች እና ድሆች ነበሩ። ኢየሱስ በኅብረተሰቡ ውስጥ ትልቅ ቦታ ለሌላቸው ሰዎች ማለትም ድሆች፣ ለምጻሞች፣ መበለቶች፣ መጻተኞችና ልጆች እንክብካቤሰን አሳይቷል (ሉቃስ 7፥22)። ለድሆች የምስራች ልናገር መጣሁ አለ። ወንጌል የተጨቆኑትን ነጻ እንደሚያወጣ ተናግሯል (ሉቃስ 4፥18-19)።
ከቤተክርስቲያን የመጀመሪያ ዘመን ጀምሮ አማኞች በማህበረሰባቸው ውስጥ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል። የተጣሉ ልጆችን ወደ ቤታቸው ወስደዋል፣ ባሮችን አሳልፈዋል እንዲሁም የታመሙትን ረድተዋል። ማህበረሰቦቻቸው ዋጋ ቢስ እንደሆኑ አድርገው የሚቆጥሯቸውን ሰዎች ተንከባክበዋል።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግሥት ትምጣ ፈቃዱ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን ብለን መጸለይ እንዳለብን ተናግሯል (ማቴዎስ 6፥10)። የእግዚአብሔር መንግሥት በምድር ላይ በምትመጣበት ጊዜ ጭቆና ሁሉ እንደሚያበቃ እናውቃለን። እስከዚያው ድረስ በየቦታው ለተጨቆኑ ሰዎች እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባልን መጸለይ አለብን።
ለአብዛኛዎቹ ቡድኖች ይህ ርዕስ ብዙ ውይይት ይፈጥራል። አንዳንድ ተማሪዎች ስላጋጠማቸው ወይም ስላዩት ነገር ጠንካራ ስሜት ሊኖራቸው ይችላል።
► እያንዳንዱ ሰው ለእግዚአብሔር ያለውን ዋጋ ካስታወስክ ለሌሎች ብሔረሰቦች ያለህ አመለካከት እንዴት ይለወጣል?
► ስለ ሰው ዋጋ አሁን ባወቅከው ምክንያት በተለየ መንገድ ብታደርግ የምትመኘው ነገር ምንድን ነው? ሌሎች ስላደረጉት ነገር ቁጣን ከመግለጽ ይልቅ ተማሪዎች የራሳቸውን ቁርጠኝነት እንዲያካፍሉ ያበረታቷቸው።
► የሰው ዋጋ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት እንዴት ሊነካው ይገባል?
የሰማይ አባት
በአምሳልህ ስለሰራኸን እናመሰግናለን። ሰዎችን ሁሉ እንዳከብር እርዳኝ። በሰዎች ላይ ካለኝ ጭፍን ጥላቻ እና ቅሬታ ንስሀ እንድገባ እርዳኝ።
በአለም ዙሪያ በዘር፣ በፆታ፣ በእድሜ ወይም በሌላ ባህሪ ምክንያት በደል ለሚደርስባቸው ፍትህ እንድታመጣ እጸልያለሁ።
ለተጨቆኑ ሰዎች እንድከላከል እና ማህበረሰቤን ለሁሉም ፍትሃዊ ለማድረግ እንድሰራ እርዳኝ። ቤተክርስቲያናችንን እና እያንዳንዱ አማኝ ለአለም የአንተን ፍቅር በልዩ መንገድ እንዲያሳዩ እርዳቸው።
አሜን
(1) ቤተክርስቲያኒቱ በማኅበረሰቧ ውስጥ የሰዎችን አያያዝ ለመቀየር እግዚአብሔር ስለሰጣት ኃላፊነት ጻፍ።
ቤተክርስቲያንህ ምን ማድረግ አለባት?
አማኞች እንደ ግለሰብ ምን ማድረግ አለባቸው?
እርስዎ ምን ያደርጋሉ?
(2) ዘዳግም 24፥10-22 አጥኑ። የሰዎችን ዋጋ የሚያሳዩ ትዕዛዞችን ይዘርዝሩ። የእያንዳንዱን ትዕዛዝ ዓላማ ያብራሩ።
13 lessons · አማርኛ
Your print request has been recorded. Your download should begin shortly.
Download Print-Ready FileFree to print for ministry use. No changes to content, no profit sales.
SGC exists to equip rising Christian leaders around the world by providing free, high-quality theological resources. We gladly grant permission for you to print and distribute our courses under these simple guidelines:
All materials remain the copyrighted property of Shepherds Global Classroom.
Questions? info@shepherdsglobal.org
Total
$21.99Added to Cart!
By submitting your contact info, you agree to receive occasional email updates about this ministry.
Download audio files for offline listening
No audio files are available for this course yet.
Check back soon or visit our audio courses page.
Share this free course with others