የትምህርት ዓላማዎች
በዚህ ትምህርት መጨረሻ ተማሪው የሚከተሉትን ማድረግ ይኖርበታል፦
(1) እግዚአብሔር በመንግስት ላይ ያስቀመጠውን ሃላፊነት እና ውስንነት መረዳት።
(2) ከመንግስት ጋር በተያያዘ መፅሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎችን እና መርሆችን ማክበር።
(3) በማህበረሰቡ ውስጥ ለጽድቅ ተጽእኖ ፈጣሪ ለመሆን ቃል መግባት።
Lesson
Playlist
Search through all lessons and sections in this course
Searching...
No results found
No matches for ""
Try different keywords or check your spelling
1 min read
by Stephen Gibson
በዚህ ትምህርት መጨረሻ ተማሪው የሚከተሉትን ማድረግ ይኖርበታል፦
(1) እግዚአብሔር በመንግስት ላይ ያስቀመጠውን ሃላፊነት እና ውስንነት መረዳት።
(2) ከመንግስት ጋር በተያያዘ መፅሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎችን እና መርሆችን ማክበር።
(3) በማህበረሰቡ ውስጥ ለጽድቅ ተጽእኖ ፈጣሪ ለመሆን ቃል መግባት።
William Wilberforce (ከ1759-1833) የብሪቲሽ ፓርላማ አባል ሲሆን ከዚያም ወደ አማኝነት የተቀየረ እና ባርነትን፣ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን እና የድሆችን እንግልት መቃወም ጀመረ። ከአፍሪካ ምርኮኞችን በመውሰድ በመላው የብሪቲሽ ኢምፓየር ይሸጥ የነበረውን የባሪያ ንግድ የሚያቆም ህግ ለማውጣት ለ20 አመታት ሰርቷል። ሌሎች ስለ ጉዳዩ ምንም ደንታ የሌላቸው ስለሚመስሉ ብዙ ጊዜ ይበሳጭ ነበር። አንድ ጊዜ አብላጫውን የፓርላማ አባላት ህጉን እንዲደግፉ ተስማምተው ነበር ነገር ግን ተቃዋሚዎች የተወሰኑ አባላትን የቲያትር ትኬቶችን በመስጠት የፓርላማውን ስብሰባ እንዲያቋርጡ አድርጓቸዋል እና ህጉ አልፀደቀም ነበር። በ1807 የባሪያ ንግድን የሚከለክል ህግ ቢወጣም ነገር ግን ባርነት እራሱ ገና ህገወጥ አልነበረም። Wilberforce ባርነትን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ዘመቻውን ቀጠለ። በ1833 ባብዛኛው የብሪቲሽ ኢምፓየር ውስጥ ባርነት አብቅቷል። Wilberforce ሕጉ እንደሚያጸድቅ ዜና ካገኘ ከሶስት ቀናት በኋላ ሞተ።
አማኞች ከመንግሥቶቻቸው ጋር በነበራቸው ግንኙነት ውስጥ ብዙ ዓይነት ልዩነት አለ። በታሪክ አንዳንድ ጊዜ እና ቦታዎች ከመንግስት ጋር የተሳሰረች ብሄራዊ ቤተክርስቲያን ነበረች። በሌላ ጊዜና ቦታ መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱን ሕገወጥ አድርጎ ያሳድዳታል። ሰዎች የፈለጉትን ሃይማኖት በነፃነት እንዲከተሉ የሚፈቅዱ ሀገራት አሉ፤ መንግሥታቸውም ለየትኛውም ሃይማኖት እንደማይደግፉ ይናገራሉ።
በአማኞች እና በመንግስት መካከል ያለው ግንኙነት ብዙ አስቸጋሪ ጥያቄዎችን ይፈጥራል። አንዳንድ ጊዜ በአንድ ቦታ ያለች ቤተክርስቲያን መንግሥት በጣም በሚለያይባቸው ሌሎች የዓለም ክፍሎች ሊኖር የማይችል ከመንግሥት ጋር የሚሆን ግንኙነት ትፈጥራለች።
ይህ ትምህርት ለእያንዳንዱ ጥያቄ መልስ አይሰጥም ወይም የክርስቶስ ተከታይ በማንኛውም ሁኔታ ምን ማድረግ እንዳለበት አያብራራም ነገር ግን አማኝ ከመንግስት ጋር ስላለው ግንኙነት አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎችን እንመለከታለን።
► አንድ ተማሪ ለብድኑ ሮሜ 13፥1-7ን ያንብብ። በዚህ ክፍል ውስጥ ስለ መንግስት ምን መግለጫዎች ታያለህ?
እግዚአብሔር የሰውን መንግሥት እንዳቋቋመ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። እግዚአብሔር መንግሥት እንዲኖር ይፈልጋል እናም የሰውን መንግሥት ለመታዘዝ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው በእግዚአብሔር ላይ እያመፀ ነው (ሮሜ 13፥1-2)።
► በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት የመንግሥት ዓላማ ምንድን ነው?
የመንግስት አንዱ አላማ ህግን በማስከበር መጥፎ ባህሪን መቅጣት ነው (ሮሜ 13፥3)። ገዥው እግዚአብሔርን የሚያገለግል እና ሕግ የሚጥሱ ሰዎችን በሚቀጣበት ጊዜ የእግዚአብሔርን ዓላማዎች ይፈጽማል (ሮሜ 13፥4)።
► አንድ ተማሪ ለብድኑ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥1-2 ያንብብ።
ጸጥታ የሰፈነበት እና ሰላማዊ ኑሮ እንድንኖር በመንግስት ውስጥ ላሉ ሰዎች መጸለይ አለብን። ይህም የሚነግረን አንድ መንግስት በሚፈልገው መልኩ ሲሰራ የህብረተሰቡን ሰላም እንደሚጠብቅ ነው።
► ማቴዎስ 5፥13-16ን አንብብ። ኢየሱስ ጨውና ብርሃን እንድንመስል ሲነግረን ምን ማለቱ ነበር?
አንዳንድ ሰዎች የዓለም መንግሥታት በክርስቲያናዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች ስለማይገዙ የክርስቶስ ተከታዮችን መምረጥ ወይም የመንግሥት ቦታ መያዝ የለባቸውም ብለው ያምናሉ። አንዳንድ ክርስቲያኖች ማህበረሰቡ በጣም ብልሹ ስለሆነ ቤተክርስቲያን በህብረተሰቡ ውስጥ የማትገባ የተለየች ማህበረሰብ መሆን አለባት ብለው ያምናሉ።
ነቢዩ ኤርምያስ በእግዚአብሔር በማያምኑ ማኅበረሰብ ውስጥ ለመኖር ከአገራቸው ለተወሰዱ አይሁዶች ጻፈ። በዚያ በፈቃዳቸው አልነበሩም። በእግዚአብሔር የሚያምን በህብረተሰብ ውስጥ ከመሳተፍ የሚታቀብበት ምክንያት ቢኖረው በእርግጥ እነዚህ አይሁዶች አላቸው። እነርሱ ያለፍላጎታቸው እዚያ ነበሩ፣ የህብረተሰቡ ሃይማኖት እግዚአብሔርን የማያውቅ ነበር፣ መንግስቱም ጨቋኝ እና ህዝባቸውን ያጠፋ ነበር እና አይሁዶች ከዚያ የሚወጡበትን ቀን እየጠበቁ ነበር።
ነገር ግን እግዚአብሔር ለእነዚህ ሰዎች በነቢዩ የሰጠውን መልእክት አድምጡ፡-
ተማርካችሁ ለሄዳችሁባት ከተማ ሰላምና ብልጽግናን እሹ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸልዩላት፤ ምክንያቱም እርሷ ብትበለጽግ እናንተም ትበለጽጋላችሁ (ኤርምያስ 29፥7)።
ሻሎም፤ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው የዕብራይስጥ ቃል የሚያመለክተው ሰላምን ብቻ ሳይሆን ከሰላም ጋር የሚመጡትን በረከቶች ነው። የእግዚአብሔርን በረከቶች ያመለክታል። እነዚህ የእግዚአብሔር አገልጋዮች እነዚያን በረከቶች ስለ እርሱ ምንም ወደማያውቀውና ሕዝቡን ወደ ሚያሳድዱ ኃጢአተኛ ማኅበረሰብ ውስጥ ለማምጣት ሲሞክሩ የእግዚአብሔርን በረከቶች ያገኛሉ።
እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ሰዎች ማህበረሰባቸው የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲያከብር እርሱም ይባርካቸው ዘንድ ተጽዕኖን ማድረግ አለባቸው። ወንጌልን ማካፈል ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን መርሆች በሁሉም ሁኔታዎች እና ውሳኔዎች ላይ ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው።
መንግስት እና ማህበረሰብ በእግዚአብሔር ቃል መቀረፅ አለባቸው። ከእግዚአብሔር ከተገለጠው እውነት የሥነ ምግባር (የትክክለኛ ተግባራት ደንቦች)፣ ከሥነ ምግባር ፖለቲካ (መንግሥት ለፍትሕና ለነጻነት)፣ ከዚያም ኢኮኖሚክስ (ሀብትን ማስተዳደር) መምጣት አለበት። ስለዚህ ትክክለኛው ሥርዓት እውነት ነው፣ ከዚያም ሥነምግባር፣ ከዚያም ፖለቲካ፣ ከዚያም ኢኮኖሚክስ ነው።
1. መፅሐፍ ቅዱስ
2. ሥነ ምግባር
3. ፖለቲክስ
4. ኢኮኖሚክስ
የሰው ልጅ ማህበረሰብ ተፈጥሯዊ ዝንባሌ ያንን ስርአት መቀየር ነው። ሰዎች ለግል ኢኮኖሚያቸው ቅድሚያ ይሰጣሉ፣ ከዚያም ፍትህና ነፃነት ማጣት ቢኖርባቸውም የፈለጉትን የሚሰጧቸውን መሪዎችና ሕጎች ይደግፋሉ፣ ከዚያም ከሚሠሩት ጋር እንዲጣጣም ሥነ ምግባራቸውን መሥርተው ከዚያም ጸባያቸውን ለማፅደቅ ሃይማኖትን ይነድፋሉ። ስለዚህ የተለመደው ሥርዓት ኢኮኖሚክስ፣ ከዚያ ፖለቲካ፣ ከዚያ ሥነምግባር፣ከዚያም ሃይማኖት ነው።
1. ኢኮኖሚክስ
2. ፖለቲካ
3. ሥነ ምግባር
4. ሀይማኖት
ይህ ዓይነቱ ሃይማኖት የተቀረጸው በተሳሳተ መርሆች በመሆኑ ብዙ እውነት ይጎድለዋል።
ቤተክርስቲያን የህብረተሰቡን ኃጢአት በመቃወም ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቡ ምን መሆን እንዳለበት በማስረዳትና በማሳየት ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት መቆም አለባት። አማኞች ህብረተሰቡ ምን ማድረግ እንዳለበት ማብራራት እና ማሳየት ካልቻሉ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የማይቀበሉ ሰዎች እርሱን ተግባራዊ ማድረግ እንደማይችሉ መጠበቅ አለብን።
አማኞች ማህበረሰባቸውን ብቻ መተቸት የለባቸውም። አማኞች የህብረተሰባቸው አካል መሆን አለባቸው። አማኞች እራሳቸውን በማኅበረሰባቸው ውስጥ በንቃት ማሳተፍ እና የፍትህ ጠበቃ መሆን አለባቸው። አማኞች ሁልጊዜ በሁሉም ድርጊታቸው ሥነ ምግባራዊ መሆን አለባቸው እና በዚህም ሌሎችን ለጽድቅ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። የክርስቲያን መሠረታዊ ሥርዓቶችን ሳይጥሱ ይህን ማድረግ እስከቻሉ ድረስ በመንግሥትና በህብረተሰቡ ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ ድርጅቶች ውስጥ መሳተፍ አለባቸው። ከተፈቀደላቸው ደግሞ ክርስቲያናዊ ባህሪ እንዲኖራቸው በጣም ቅርብ የሆኑትን ለቢሮ እጩነት መምረጥ እና መደገፍ አለባቸው።
► በመፅሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ ተመርኩዞ ውሳኔ ከማድረግ ይልቅ ለኢኮኖሚ ደህንነት ሲባል ውሳኔ እንድታደርግ ማኅበረሰቡ በቤተክርስቲያን ላይ የሚያሳድረው ጫና ምሳሌ ምንድን ነው?
በታሪክ ውስጥ ያሉ አማኞች መንግስታቸው የተለያዩ መርሆችን ሲከተል በዚያን ጊዜ እንዴት የክርስትናን መርሆች መከተል እንዳለባቸው ለማወቅ ታግለዋል። አንዳንድ ጊዜ ግጭቱ ከባድ ነው እና አማኞች መንግስት የሚፈልገውን ነገር ማድረግ ባለመቻላቸው በእምነታቸው ምክንያት ይሰቃያሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ መንግሥት የሚፈልገውን ግብር እንድንከፍል ይነግረናል (ሮሜ 13፥7፣ ማቴዎስ 22፥21)።
መጽሐፍ ቅዱስ የሀገራችንን ሕግ እንድንታዘዝ ይነግረናል (ቲቶ 3፥1)። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ የእግዚአብሔር ትእዛዛት ከሰው ሕግ ጋር በሚጋጭበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔርን መታዘዝ እንዳለብን ይነግረናል (ሐዋርያት ሥራ 5፥29)።
መንግስት ሰዎች ወታደር ሆነው ፍትሃዊ ባልሆነ ምክንያት እንዲዋጉ ሊጠይቅ ይችላል። የህዝብ ቁጥር መብዛትን ለመቀነስ መንግስት የህፃናትን ሞት ሊጠይቅ ይችላል። መንግስት ህዝቡ ከጎሳ ባርነት ጋር እንዲተባበር ሊጠይቅ ይችላል።
አንዳንድ ጊዜ ጉዳዮቹ ስለ አምልኮ ናቸው። የክርስቶስ ተከታዮች የቤተሰባቸውን ወይም የነገዳቸውን አማልክትን በማያመያልኩበት ጊዜ ስደት ሊደርስባቸው ይችላል። አማኞች የተለየ ሃይማኖት በመንግስታቸው ሲደገፍ ሊሰደዱ ይችላሉ።
አንዳንድ ሀገራት የወንጌል ስርጭት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትን የሚቃወሙ ህጎች አሏቸው። አማኞች ወንጌልን ሲሰብኩ ይሰደዳሉ። አንዳንድ ሀገራት ልጆቻቸውን ስለ እግዚአብሔር የሚያስተምሩ ወላጆችን ይቀጣሉ።
በገዥዎች የተሰጡ ኢፍትሐዊ ትእዛዞችን ያልታዘዙ የእምነት ሰዎችን የሚያሳዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎች አሉን። ዳንኤል ጸሎት ሕገወጥ በሆነበት ጊዜም እንኳ መጸለዩን ቀጠለ (ዳንኤል 6፥10)። የዳንኤል ሦስቱ ወዳጆች የንጉሡን ጣዖት ለማምለክ ፈቃደኛ አልሆኑም (ዳንኤል 3፥16-18)። እስራኤላውያን አዋላጆች ፈርዖንን የእስራኤልን ሕፃናት እንዲገድሉ ባዘዛቸው ጊዜ አልታዘዙም (ዘጸአት 1፥17)።
በታሪክ ውስጥ አማኞች ሕገ-ወጥ ቢሆንም እንኳ ወንጌልን ሠርተዋል። አማኞች በሕገወጥ መንገድ መጽሐፍ ቅዱሶችን ይዘው ከሀገር ድንበሮች አቋርጠዋል። አማኞች በስውር ለማምለክ ይሰበሰባሉ። አማኞች ያለአመጽ ፅንስ የሚያስወርዱ ክሊኒኮችን አግደዋል። አማኞች ያመለጡ ባሪያዎችን ረድተዋል።
አብዛኞቹ አማኞች ሕይወታቸውን በሰላም መኖርን ይመርጣሉ እና ከእንደዚህ አይነት ውሳኔዎች ጋር መጋፈጥ አይፈልጉም። ነገር ግን አማኞች የስነምግባር ችግር ካጋጠማቸው መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ቢሆንም ትክክለኛውን ነገር ማድረግ አለባቸው። ኢፍትሃዊነትን ለመከላከል ወይም ወንጌልን ለመካፈል እድሉ ካላቸው እርምጃ ለመውሰድ ወይም ላለማድረግ ሲወስኑ ከባድ ውሳኔ እያደረጉ ነው።
► በአገርዎ ውስጥ ላለ አማኝ ሊደርስ የሚችለውን ሕጋዊ አጣብቂኝ መግለፅ ይችላሉን?
አንድ ፓስተር በባዕድ አገር ይጓዝ ነበር። ትክክለኛ ሰነዶች ነበሩት ነገር ግን ብዙ ጊዜ ፖሊሶች አስቁመው ትንሽ ገንዘብ ይጠይቁት ነበር። ገንዘብ ካልሰጣቸው ጉዞውን ያዘገዩና እና ያስቸግሩት ነበር።
► ፓስተሩ በዚህ ሁኔታ ምን ማድረግ አለበት?
ጉቦ አንድን ነገር እንዲፈቅድ ተጽዕኖ ለማድረግ ስልጣን ላለው ሰው የሚከፈል ገንዘብ ነው። ሰው ማድረግ የማይገባውን ነገር እንዲያደርግ ጉቦ መስጠት ስህተት ነው (ዘዳግም 16፥19)። ለምሳሌ አንድ ሕንፃ ወይም አውቶሞቢል ተገቢውን መስፈርት ካላሟላ እውነት ያልሆነ ነገር እንዲፈርም ለተቆጣጣሪው ጉቦ መስጠት ስህተት ነው። በግፍ እንዲፈርድ ለዳኛ ወይም ለፖሊስ ጉቦ መስጠት ስህተት ነው።
አንዳንድ ጊዜ በሥልጣን ላይ ያለ ሰው ማድረግ የሚገባውን ለማድረግ ጉቦ ይጠይቃል። በዚህ ጊዜ የሚከፍለው ሰው ስህተት እንዲሠራ እየከፈለው አይደለም። ባለሥልጣኑ እንዲሰጠው መጠየቁ ስህተት ነው (ሉቃስ 3፥14) ነገር ግን የሚከፍለው ሰው ምርጫ ላይኖረው ይችላል። ለምሳሌ ሊፈቀድ የሚገባውን ነገር ፈቃድ ማግኘት ወይም የንፁህ ሰውን ነፃነት ማግኘት ነው። አንዳንዴ ጉቦ እንደ ዘረፋ ነው። ዘረፋ ስህተት ነው ነገር ግን ተጎጂውን አንወቅስም።
መፅሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ስንመለከት እግዚአብሔር ጉቦ የሚቀበሉትን እንደሚኮንን ነገር ግን ለመክፈል ለሚገደዱት መሐሪ መሆኑን ያሳያል (ዘጸአት 18፥21፣ ዘጸአት 23፥8፤ ዘዳግም 10፥17፣ ዘዳግም 16፥19፣ ዘዳግም 27፥25)። አማኞች ለምቾታቸው ሲባል በፍፁም ጉቦ መክፈል የለባቸውም ነገር ግን በባለስልጣኖች ሲገደዱ ጥፋተኞች አይደሉም።
► የተሳሳተ ጉቦ ምሳሌ ምንድን ነው?
ብዙ የክርስቶስ ተከታዮች ለሀገራቸው ወታደር ሆነው ማገልገል ስህተት እንደሆነ ያምናሉ። እምነታቸውን በተወሰኑ መፅሐፍ ቅዱሳዊ መግለጫዎች ላይ ይመሰረታሉ። ኢየሱስ አንድ ሰው ሲመታን ሌላውን ጉንጭ ማዞር እንዳለብን ተናግሯል (ማቴዎስ 5፥39)። ኢየሱስ አገልጋዮቹ እንደማይጣሉ ተናግሯል ምክንያቱም መንግሥቱ ከዚህ ዓለም አይደለችም (ዮሐንስ 18፥36)። ሐዋርያው ጳውሎስ የጦር መሣሪያችን ሥጋዊ አይደለም (2ኛ ቆሮንቶስ 10፥4) ብሏል። እነዚህ ክርስቲያኖች በሌሎች ሰዎች ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ጥቃት ስህተት ነው ብለው ያምናሉ። ብዙዎቹ የሚኖሩት መንግስት ነፃነትን በማይፈቅድባቸው እና አማኞችን በሚያሳድድበት ሀገራት ነው።
ሌሎች ክርስቲያኖች እንደ ወታደር አገራችንን ለመከላከል ፈቃደኛ መሆን እንዳለብን ያምናሉ። መፅሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር መንግሥትን እንዳቋቋመና መንግሥትም ትክክል ያልሆነውን የሚያደርጉትን ለመቅጣት የጦር መሣሪያ መጠቀም እንደሚችል ይናገራል (ሮሜ 13፥4)። እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ቤተሰቡን ለመጠበቅ እንደሆነ ግልጽ ይመስላል እና ስለዚህ ሰዎች በጦር ሠራዊት መልክ ቤተሰቦቻቸውን ከጥቃት ለመጠበቅ መዘጋጀት ተፈጥሯዊ ይመስላል። አንድ ወታደር መጥምቁ ዮሐንስን እንዴት ንስሐ እንደሚገባ ሲጠይቀው ዮሐንስ ጉቦ እንዳይወስድ ወይም ግላዊ ግፍ እንዳይፈጽም ነገረው ነገር ግን ከሠራዊቱ እንዲወጣ አልነገረውም (ሉቃስ 3፥14)። ኢየሱስ ሌላውን ጉንጭ ያዙሩ ሲል ራሳችንን ከጥቃት መጠበቅ የለብንም ማለቱ ሳይሆን ፊት ላይ በመምታት አጸያፊ ድርጊትን ለማጥቃት ራሳችንን እንዳንበቀል ነው። አገልጋዮቹ ለእርሱ ምድራዊ መንግሥትን ለመመሥረት እንደማይዋጉ ተናግሯል ምክንያቱም እርሱ መንግሥቱን በዚህ መንገድ አይመሠርትም። መንግስት የእግዚአብሔር ሃሳብ ከሆነ እና መንግስት ህዝቡን መከላከል ካለበት አማኞች መንግስታቸውን ለማገልገል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማገዝ ተገቢ ነው።
በዘመናት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በብዙ አገሮች ውስጥ ያሉ ብዙ አማኞች በጦር ኃይሎች ውስጥ በውጊያም እንኳን ሳይቀር ሕዝባቸውን አገልግለዋል፤ ምክንያቱም ሀገራቸውን ከክፉ ጥቃት ለመከላከል የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ስላመኑ ነው።
በዓለም ዙሪያ ያሉ ክርስቲያኖች በወታደራዊ አገልግሎት ጉዳይ ላይ አይስማሙም። አንድ ሰው መፅሐፍ ቅዱስን እና ምክንያትን በጸሎት በመመርመር ከዚያም የራሱን እምነት በታማኝነት መከተል አስፈላጊ ነው።
► በአገርዎ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት የውትድርና አገልግሎት ጥያቄን እንዴት ይመለከታሉ?
አብዛኞቹ አማኞች በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አስተያየት አላቸው። በተለያዩ ጊዜያት እና ቦታዎች የነበሩ የክርስቶስ ተከታዮች በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ ሁሉም እንዳልተስማሙ መረዳት ያስፈልጋል። የሌሎችን ሃሳብ ከመፍረድ መቆጠብ አለብን።
► በአገራችን በአብያተ ክርስቲያናት እና በመንግስት መካከል ያለውን የተለመደ ግንኙነት እንዴት መገምገም አለብን? የሆነ ነገር መለወጥ አለበትን?
የሰማይ አባት
ጥበቃ እና ነፃነትን ለመስጠት መንግስትን ስለነደፍክ አመሰግናለሁ። የሰው ልጅ መንግስት አለፍጽምና ቢኖርም ለአንተ ታማኝ እንድሆን እርዳኝ።
ሌሎችን የመጠበቅ እና በማህበረሰቤ ላይ ተጽእኖ የማድረግ ሀላፊነቴን እንድወጣ እርዳኝ።
የመንግሥትህን መምጣት በሙላት እንጠባበቃለን።
አሜን
(1) መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር በሕዝቦቹ ሕይወት ውስጥ ያለውን ዓላማ ለመፈጸም በመንግሥት ባለሥልጣናት አማካኝነት እንደሠራ የሚገልጹ ብዙ ዘገባዎችን ይዟል። ምሳሌ 21፥1 እንዲህ ይላል “የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እርሱም እንደ ቦይ ውሃ ደስ ወዳሠኘው ይመራዋል”። ለማጥናት ከእነዚህ ክፍሎች ውስጥ አንዱን ይምረጡ፦
ዘፍጥረት 41፥14-49፣ ዘፍጥረት 42፥1-3፣ ዘፍጥረት 45፥4-7
አስቴር 4፣ 7-8
ነህምያ 1-2
ከላይ በተጠቀሱት ምንባቦች ዙሪያ የራስዎን ምልከታ ይፃፍ፦
በእግዚአብሔር ሕዝቦች ሕይወት ውስጥ ምን መሆን አለበት?
እግዚአብሔር ዓላማውን ለመፈጸም ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌለውን ገዥ የተጠቀመው እንዴት ነው?
እግዚአብሔር ዓላማውን ለማስፈጸም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለውን ሰው የተጠቀመው እንዴት ነው?
(2) ከእነዚህ ርዕሶች ውስጥ አንዱን ይምረጡ፦
ክርስቲያናዊ ተጽእኖ
ክርስቲያኖች እና የሰው ሕጎች
ጉቦ
ወታደራዊ አገልግሎት
ከርዕስዎ ጋር በተገናኘ በዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኙትን የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይመልከቱ። ለዚህ ርዕሰ ጉዳይ መፅሐፍ ቅዱሳዊ አቀራረብ ነው ብለው የሚያስቡትን በገጽ ይጻፉ።
13 lessons · አማርኛ
Your print request has been recorded. Your download should begin shortly.
Download Print-Ready FileFree to print for ministry use. No changes to content, no profit sales.
SGC exists to equip rising Christian leaders around the world by providing free, high-quality theological resources. We gladly grant permission for you to print and distribute our courses under these simple guidelines:
All materials remain the copyrighted property of Shepherds Global Classroom.
Questions? info@shepherdsglobal.org
Total
$21.99Added to Cart!
By submitting your contact info, you agree to receive occasional email updates about this ministry.
Download audio files for offline listening
No audio files are available for this course yet.
Check back soon or visit our audio courses page.
Share this free course with others